አዲሱ የጀርመን የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ ሕግ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 15.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አዲሱ የጀርመን የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ ሕግ

የጀርመን ተጣማሪ መንግሥት በአዲስ የስደተኞች ረቂቅ ሕግ ጉዳይ ትናንት ስምምነት ላይ ደርሷል። ረቂቅ ሕጉ፣ የስደተኞችን ሥራ የማግኘት ዕድል እንደሚያሰፋና እንደሚያፋጥን ተገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:14
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:14 ደቂቃ

የጀርመን የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ ሕግ

በሌላ በኩል በረቂቁ ጀርመን ተገን የተሰጣቸው ስደተኞች ከኅብረተሰቡ ጋር ተዋሕደው እንዲኖሩ በተቀረጸው መርሃ ግብር የተካተቱትን መስፈርቶች ካላሟሉ መንግሥት የሚሰጣቸው ድጋፍ እንደሚቀንስም ተጠቅሷል። ቀጣዩ ዘገባ የረቂቅ ህጉን ምንነትና አላማ ይቃኛል።
የጀርመን ተጣማሪ መንግሥት ትናንት ስምምነት ላይ የደረሰው ባለፈው ዓመት ጀርመን የገቡ 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ስደተኞች ከኅብረተሰቡ ጋር ተዋሕደው ለመኖር ያግዟቸዋል በተባሉ ልዩ ልዩ እርምጃዎች ላይ ነው። ተጣማሪው መንግሥት የተስማማበት በረቂቅ ደረጃ የቀረበው ይኽው ሕግ የሕግ ባለሙያና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ይልማ ይፍራሸዋ እንዳሉት በመጀመሪያ ደረጃ ከቀድሞው በተለየ የተገን ጠያቂዎችን መኖሪያ የሚገድብ ነው።
መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ግጭትና ግድያን ሸሽተው ጀርመን የመጡ ስደተኞች የተገን ጥያቄያቸው አፋጣኝ መልስ

እንዲያገኝ፣ የኤኮኖሚ ስደተኞች የሚሏቸው ደግሞ በተቻለ ፍጥነት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይፈልጋሉ። እዚህ መኖር የተፈቀደላቸው ደግሞ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሠሩ የመንግሥት ድጎማ ተቀባይ እንዲሆኑ አይፈለግም።
ስደተኞች የቋንቋ ትምህርት ለመጀመር እንደ ከዚህ በፊቱ ሶስት ወር መጠበቅ የለባቸውም። አዲሱ ሕግ ጊዜውን ወደ 6 ሳምንት አሳጥሮታል። ሕጉ ታሪካዊ ሊባል የሚችል ለውጥም ተካቶበታል። ዶክተር ለማ እንደሚያስረዱት ረቂቁ ከዚህ ቀደም የተመናመነ የነበረውን፣ ለስደተኞች ክፍት የሥራ ቦታ የማግኘት እድልንም ያሰፋል።
የስደተኞችን መብት እና ግዴታዎች የተዘረዘሩበት ይኽው ሕግ ይላሉ ዶክተር ለማ በዋነኛነት ወደ ጀርመን የሚመጣውን ስደተኛ ቁጥር ለመቀነስ ያለመመም ነው።
ረቂቅ ሕጉ ለሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመቅረቡ በፊት ከጀርመን ፌደራዊ ክፍላተ ሃገራት መሪዎች ጋር ውይይት ይደረግበታል።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic