አዲሱ የዼንጤ ቆስጤ ቤተክርስቲያን በአፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 21.09.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አዲሱ የዼንጤ ቆስጤ ቤተክርስቲያን በአፍሪቃ

አዳዲሶቹ ቤተክርስቲያናት፤ቀድመው ከነበሩት የካቶሊክና የዼንጤቆስጤ ቤተክርስቲያናት ጭምር በበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተከታዮችን የመሳባቸው ምክንያቱ ምን ይሆን?

እኛ የክርስቶስ ተከታዮች ነን

እኛ የክርስቶስ ተከታዮች ነን

የዶቸቬሌው ቶማስ ሞሽ ናይጄሪያ ድረስ በመጓዝ እነዚህን ቤተክርስቲያናት ጎብኝቷል።በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ዘወትር እሁድ ይሰባሰባሉ።ራሳቸውንም በእምነት ጎዳና የእግዚአብሔር መዘውሮች ብለው ነው የሚጠሩት።የተለያዩ መዝሙርች፣በሀይለኛ ድምጽ የሚነገሩ ስብከቶች፣ርኩስ መንፈስን ለማባረር የሚደረግ ጥረት እና በተዐምር ደዌን መፈወስ፤የእምነቱ አካላት ናቸው ይለናል ቶማስ ሞሽ።

ለምሳሌም ከተዓምራቶቹ መካከል ሲጠቅስልን፤ናይጀሪያዊቷ አዩማህ ሆንዴህ ያጋጠማትን ያነሳል።አዩማህ በአንድ የምግብ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ተሰልፋ ቆማለች።እናም በድንገት አንድ ወጣት ልጅ ይመጣና ይገፈትራታል።በወቅቱ ከልጁ ጋር እንኪያሰላምታ መግጠም አልፈለገችም ነበርና ወደሌላኛው ሰልፍ አቀናች።ታዲያ በዚያች ቅጽበት የሚገርም ነገር ተከሰተ።አዩማህ መጀመሪያ የነበረችበት ሰልፍ ውስጥ ያሉት ሰዎች ድንገት በመጣው ዘራፊ ሠለባ ሆኑ።በወቅቱ ዘራፊው አዩማህ ላይ ምንም ያደረሰው ጉዳትም ሆነ ዘረፋ አልነበረም።

ይህ አዲስ አቀራረብ ያለው የዼንጤ ቆስጤ እምነት ከትንንሽ መንደሮች አንስቶ ዘመናዊ በሆኑ የእምነት ማዕከላት፣በዮኒቨርሲቲዎች፣እና በገበያ ማዕከላት ጭምር በፍጥነት እየተስፋፉ ነው።ይሁንና ግን እስልምናን እንደባላንጣ የመመልከት አዝማሚያ ስላለው አደገኛ ነገር ሊደቅን እንደሚችልም ተፈርቷል።በጀርመን፤ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የሚሽን አካዳሚ ዳይሬክተር የሆኑት ኤርሐርድ አምፕሀውሰን ፍራቻቸውን እንዲህ ይተነትኑታል።

እንደኔ እንደኔ በርካቶቹ ቤተክርስቲያናት መስቀሎቻቸውን ይዘው ወደ ሰሜን ባያቀኑ ይበጃል(ሠሜን ናይጀሪያ በርካታ ሙስሊም የሚኖርበት ነው)እዚያ ሁኔታው አደገኛ ነው የሚሆነው።በተለይ በእስልምና እና በክርስትና መካከል የማይበርድ ግጭትን ሊቀሰቅስ ይችላል።የእስልምና እምነት ተከታይ በሚበዛባት ናይጀሪያ እንዲህ ያለ ዘመቻ፤ከዚህ ቀደም የተከሠተውን አይነት ጅምላ ጭፍጨፋ ሊያስከትልም ይችላል በማለት ዳይሬክተሩ ፍራቻቸውን ገልፀዋል።