አዲሱ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲ | አፍሪቃ | DW | 12.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

አዲሱ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲ

የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል ፖል ማሎንግ አዲስ የተቃዋሚ ፓርቲ አቋቋሙ። ይህ የደቡብ ሱዳን የተባበረ ግንባር የሚል መጠሪ የያዘው ፓርቲ በሕገ መንግሥቱ ላይ ተሀድሶ እንዲደረግ እና አዲስ የመንግሥት ስርዓት ለማስተዋወቅ እንደሚታገል አስታውቋል። አዲሱ የተቃዋሚ ፓርቲ ለፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ተፎካካሪ የመሆኑ እድሉ ምን ያህል ነው?   

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:31

የደቡብ ሱዳን የተባበረ ግንባር

የደቡብ ሱዳን የተባበረ ግንባር የሚል መጠሪያ የያዘውን የተቃዋሚ ፓርቲ  ማቋቋማቸውን ከትናንት በስቲያ በይፋ ያስታወቁት የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል ፖል ማሎንግ በመጪው ሀምሌ በሀገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ በፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር አንፃር ለመፎካከር ይፈልጋሉ። ኪር ባለፈው ግንቦት ወር ከስልጣን ያባረሯቸው እና ወደ ኬንያ የሸሹት ማሎንግ ፕሬዚደንቱ ያለፉትን 13 ዓመታት ደቡብ ሱዳንን በደንታ ቢስነት ዘርፈዋል ሲሉ ወቅሰዋቸዋል። ከጦር ኃይሉ  ድጋፍ ይኖራቸዋል የሚባሉት አዲስ የተቃዋሚ ቡድን ያቋቋሙት ጀነራል ማሎንግ በሕዝብም ዘንድ በቀላሉ የማይታይ ድጋፍ ስላላቸው ለፕሬዚዳንት ኪር ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ በለንደን የሚገኘው የፖለቲካ ጥናት ተቋም ቻተም ሀውስ የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ አህመድ ሶሊማን ገልጸዋል።
« ፖል ማሎንግ በወረዳቸው በባህር አል ገዛል ሰፊ ድጋፍ አላቸው። ፕሬዚደንት ኪርም ከዚሁ ወረዳ  ስለሆኑ እና የጎላ ድጋፍ ስላላቸው በሁለቱ መካከል ድጋፉን በተመለከተ ጠንካራ ቅንቅን አለ። እና ይህ ማሎንግ አላቸው በሚባለው ድጋፍ የተነሳ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ከሚባሉት ተዋናዮች መካከል አንዱ መሆናቸው እንደማይቀር ግልጽ ነው። »
ይህ እውነታ እንደ ሶሌማን አስተያየት፣ የደቡብ ሱዳንን መንግሥት አያስደስትም፣ መንግሥት ማሎንግን የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ በነበሩበት ጊዜ እንደ አጥፊ እና እንደ አንድ የተቃዋሚ ቡድን አባል የኃይል ተግባር እንዲፈጸም የሚቀሰቅሱ አድርጎ ያቀርባቸው እንደነበር ሶሌማን አስታውሰዋል። እንደሚታወሰው፣ ዩኤስ አሜሪካ  ደቡብ ሱዳንን እንዳትረጋጋ ድርሻ አበርክተዋል በሚል ባለፈው መስከረም ማዕቀብ ከጣለችባቸው ባለስልጣናት መካከል ማሎንግ አንዱ ናቸው። 


ፖል ማሎንግ ሳልቫ ኪር የቀድሞ ምክትላቸውን ሪየክ ማቸርን መፈንቅለ መንግሥት ላማካሄድ አሲረዋል በሚል ምክንያት ከስልጣን ካባረሩ ከ2013 ዓም ወዲህ በቀውስ ላይ ለምትገኘው ደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማውረድ በዚህ ወር መጨረሻ ገደማ በአዲስ አበባ በታቀደው የሰላም ድርድር ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ፖል ማሎንግ ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር  በድርድር እንዲመጣ በሚፈለገው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳርፉ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። የደቡብ ሱዳን መንግሥት ስለ ማሎንግ ያለው አመለካከት ሲታሰብ  አዲሱ ፓርቲ በድርድሩ ላይ መሳተፍ መቻሉን የቻታም ሀውስ ተመራማሪ ሶሌይማን ይጠራጠሩታል።
«  ይህ እውን መሆኑን እርግጠኛ አይደለሁም። በአሁኑ ጊዜ በድርድሩ ላይ ብዙ የተቃዋሚ ቡድኖች ተሳታፊዎች ናቸው። በነዚህ ውይይቶች ላይ የሚደራደሩ የሪየክ ማቸር አይ ኦ ቡድን፣ እንዲሁም፣ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት አሉ። የአዲሱን ፓርቲ ተሳትፎ ፍላጎትን በተመለከተ እስካሁን ከመንግሥት በኩል አልሰማንም፣ ፖል ማሎንግ የውይይቱ አካል የሚሆኑበትን ጉዳይ የማስታወቂያ ሚንስትር ማይክል ማኩዌ በጣም በቁጥብነት እና በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት ብየ እገምታለሁ። »

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic