አዲሱ የእስራኤል መንግስት | ዓለም | DW | 01.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

አዲሱ የእስራኤል መንግስት

አዲሱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ የመንግስቱን አስተዳደር ከተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሁድ ኦልሜርት ዛሬ በይፋ ተረክበዋል ።

default

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነተንያሁ

ትናንት ልዩ ጉባኤ ያካሄደው የእስራኤል ፓርላማ ክኔሴት ፣ ለነታንያሁ መንግስት 69 የድጋፍና 45 የተቃውሞ ድምፅ ከሰጠ በኃላ ነታንያሁና አዲሱ ካቢኔያቸው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል ። ነታንያሁ ለእስራኤል ፓርላማ ባሰሙት ንግግር የእስራኤልን ደህንነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ከአረቡ ዓለም ጋር ሰላም ለማውረድ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል ። ይሁንና በትናንቱ ንግግራቸው ስለ እስራኤልና ፍልስጤማውያን ጎን ለጎን በሁለት መንግስትነት በሰላም ስለመኖር ግን ያሉት የለም

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኃላ