አዲሱ የትምህርት ዘመን እና ተማሪው | ባህል | DW | 24.08.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

አዲሱ የትምህርት ዘመን እና ተማሪው

አዲሱ የትምህርት ዘመን በቅርቡ ይጀምራል። በተደጋጋሚ እንደተነሳው በትምህርት ጥራቱ እና በቁሳቁስ አቅርቦቱ ላይ ጉድለት እንዳለ ይነገራል። በተለይ ከከፍተኛ ትምህርት ፍፃሜ በኋላ ምሩቃኑ በሰለጠኑበት የስራ መስክ የመስራት እድሉ ጠባብ እንደሆነ በርካታ ወጣቶች ሲገልፁ ሰንብተዋል።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Hauptcampus der Universität Addis Abeba (AAU) Thema: Die Universität Addis Abeba (AAU) ist traditionell ein Hort der politischen Opposition. Die Proteste gegen die Wahlfälschungen 2005 wurden nicht zuletzt von Studenten auf die Straße getragen. Sicherheitskräfte patroullieren derzeit verstärkt auf dem Campus Schlagwörter: Universität Addis Abeba, University of Addis Ababa (AAU), Proteste 2005, Wahl Äthiopien 2010, Ethiopia 2010

ስድስት ኪሎ ዮንቨርሲቲ አዲስ አበባ

አድማጮች ባቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ እና ጥቆማ ላይ ተመርኩዘን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መልስ አለ። አቶ ረዲ ሺፋ የትምህርት ሚንስቴር ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ከፍተኛ ኃላፊ ናቸው። «ምንም እንኳን የክረምት ጊዜ ቢሆንም የትምህርት አመራር አካላት በዚህ ዝግ በሆነው ወቅትም ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በቅድመ ዝግጅት ላይ ናቸው» ይላሉ አቶ ረዲ ሺፋ በትምህርት ሚኒስቴር በኩልም እንዲሁ ዝግጅቱ ቀጥሏል።

በፌስ ቡክ ያገኘናቸው አስተያየቶች አሉ። ሁሌ ስለ ትምህርት ጥራት እንደሚወራና ከወሬ በቀር የተሰራ ነገር እንደሌለ ይገልፃሉ። አብርሃም ፍቃደ የተባሉ አድማጫችን የሰጡን አስተያየት « የመምህራንን ኑሮ ማሻሻል ብቻ 70 ከመቶ ለውጥ ያመጣል ብዬ አምናለሁ ብለዋል። ይህ መፍትሄ ይሆን እንደው አቶ ረዲን ጠይቀናቸዋል።

GettyImages 74584876. BEKOJI, ETHIOPIA - MAY 17: Schoolchildren in class at the famous Bekoji school where many top runners were educated on May 17, 2007 in Bekoji, Ethiopia (Photo by Gary M. Prior/Getty Images).

ትምህርት ቤት በበቆጂ ከተማ

መኮንን መላኩ የተባሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ የአብረሃምን ሀሳብ ይጋራሉ። እንዲሁም የሰጡንን ሰፊ አስተያየት እንደው ለመጥቀስ ያህል። «ሁሉም የቻለውን ያድርግ (አስተማሪውም ተማሪውም):: ከሰማይ አዲስ ነገር እንዲወርድ መጠበቅ የለብንም: ወይም ካደጉ አገሮች ለኛ የሚጠቅም ነገር መጠበቅ የለብንም:: ተማሪውም ሁሌ ማማረሩን ይተው የሚችለውን ያድርግ:: ተማሪው ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ጥረት የሚያደርገውን ያህል ከዩኒቨርሲቲም ለመመረቅ ጥረት ያድርግ:: ቀልዶና ምንም ሳያጠና በአጉል ሱስ በመጠመድ ተመርቆ ዲግሪ ለመያዝ ብቻ የሚፈልገው የተማሪ ቁጥር ከአመት ወደ አመት እየጨመረ ነው:: »ብለዋል። አክለውም መምህራን ተማሪዎችን እውቀት ለማስጨበጥ የተቻላቸውን እንዲያደርጉ፤ ተማሪዎችም ዲግሪ ይዘው ከዩኒቨርሲቲ ለመውጣት ብቻ ሳይሆን ትንሽም ቢሆን አገራቸውን እንዲያገለግሉ፤ መምህራን ላይ የሚደረጉ ጫናዎች እንዲቆሙ፤

ወላጅም ልጁ ምን እየተማረ/ች እንደሆነ እንዲከታተሉ እና ከመምህራን ጋር አብረው እንዲሰሩ፣ ያልተማረ ቤተሰብም ከሆነ ከመምህራን ጋር እየተገናኘ ስለ ልጁ እንዲጠይቅ አስተያየት ሰተዋል። ለትምህርት ጥራት ከመንግስት ቀጥሎ ወላጆች ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱም አቶ ረዲም ያነሱት ሀሳብ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ከከፍተኛ ትምህርት ፍፃሜ በኋላ ምሩቃኑ በሰለጠኑበት የስራ መስክ የመስራት እድሉ ጠባብ እንደሆነ በርካታ ወጣቶች ሲገልፁ ሰንብተዋል። ለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ወደ ከፍተኛ ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ትየተማሪዎች ቁጥር ምን ያህል ነው? ለዚህ እና ሌሎችም ጥያቄዎች የትምህርት ሚንስቴር ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ከፍተኛ ኃላፊ፦አቶ ረዲ መልስ ሰተውናል።ከወጣቶች አለም ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 24.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15vdJ
 • ቀን 24.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15vdJ