አዲሱ የቅድመ -ሰው ቅሪተ- ዐፅም «አውስትራሎፒትከስ ዳይርሜዳ» | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 28.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

አዲሱ የቅድመ -ሰው ቅሪተ- ዐፅም «አውስትራሎፒትከስ ዳይርሜዳ»

ከ አራት ዐሠርተ ዓመት ገደማ በፊት ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአፋር ምድር ኀዳር በተባለው ቦታ የ 3,2 ሚልዮን ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረች፣ ድንቅነሽ ወይም ሉሲ የሚል ስያሜ የተሰጣት የቅድመ ሰው ቅሪተ ዐፅም፤ ከተገኘችበት ጊዜ አንስቶ ፤ ዝናዋ በመላው ዓለም ተስፋፋቶ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:37

አዲሱ የቅደመ -ሰው ቅሪተ- ዐፅም «አውስትራሎፒትከስ ዳይርሜዳ»

ሉሲ ለዘመናዊው ሰው «ሆሞ ሳፒዪንስ» ቀጥተኛዋ የዘር ምንጭ ናት? የቅሪተ ዐፅም አጥኝዎች ፣ምርምራቸውን እያስፋፉ እንደመምጣቸው መጠን ፤ የተለያዩ ተዛማጅ መረጃዎችን ለማግኘት ተችሏል። ለሰው ዘር ሉሲ ብቻ ቀጥተኛ ተዛማጅ እንዳልሆነች፤ እርሷ በነበረችበት ዘመን፤ ሌሎች የእርሷ ቤተ ዘመድ ዝርዮች እንደነበሩ አሁን ይፋ የወጣው ፣ የዶክተር ዮሐንስ ኃ/ሥላሴ የቅሪተ ዐፅም ግኝት ያስረዳል።

40 ዓመት ከ 6 ወር ገደማ ፤ የሰው ዘር ጥንታዊ መሠረት ፤ ወይም የቅደመ- ሰው እናት እየተባለች ስትደነቅ ኖራለች ፤ በ 2 እግሮች ቆማ ቀጥ ብላ ትራመድ እንደነበረ የተነገረላት ፣ የ 3,2 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ማስቆጠሯ የተመዘገበላት ድንቅነሽ ! ወይም ሉሲ! አሁን እርሷ ብቻ ቀዳሚዋ እንዳልነበረች የቅሪተ ዐፅም ተመራማሪዎች ተገንዝበውታል።

አፋር ውስጥ ፤ ሉሲ ከተገኘችበት ከሃዳር 35 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ ፤ ወራንሶ ሚሊ በተሰኘው ቦታ የተገኘችው ቅሪተ ዐፅም፤ ዕድሜዋ ከ 3,3-3,5 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት መሆኑ ተገልጿል። በሳይንሳዊ መጠሪያ ፣ አውስትራሎፒቲከስ-ዳዪርሜዳ ፣ በአፋርኛ «ዳዪርሜዳ» ተብላለች ፤ « የቅርብ ዘመድ» ማለት ነው ትርጉሙ። ግኝቱን ፣ መላው ዓለም ዛሬ ዋና ርእሰ ጉዳይ አድርጎታል። ስለዚህ ጉዳይ ፣ ቅሪተ ዐፅሙን ያገኙት ሳይንቲስት ዶ/ር ዮሐንስ ኃ/ሥላሴ፣ ምን ይላሉ?

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic