አዲሱ የሶማልያ ጠቅላይ ሚንስትር | ይዘት | DW | 08.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

አዲሱ የሶማልያ ጠቅላይ ሚንስትር

ከትናንት በስቲያ አብዲ ፋራህ ሺርዶን በሶማሊያ አዲስ ጠቅላይ ምኒስትር ሆነው ተሹመዋል። በቅርቡ የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ሆኖ በተመረጡት ሐሰን ሼ መሐመድ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኬኒያ ውስጥ ለረዥም ጊዜ በንግድ ዘርፉ ተሰማርተው ሰርተዋል።

Newly appointed Somalia's Prime Minister Abdi Farah Shirdon Saaid addresses the media in Somalia's capital Mogadishu October 6, 2012. Somali President Hassan Sheikh Mohamud has named Saaid as the country's new prime minister, diplomats and a government source said, the first major decision by an administration installed after over 20 years of conflict. REUTERS/Feisal Omar (SOMALIA - Tags: SOCIETY POLITICS)

አብዲ ፋራህ ሺርዶን

ከሳምንታት በፊት አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼ መሐመድ ወደ ስልጣን መምጣቸውን ተከትሎ አሸባብ ከመጨረሻው ትልቁ ይዞታው ከክስማዩ መውጣቱ ለብዙዎች መልካም ዜና ሆኖ ሰንብቷል። የፕሬዚዳንቱ ዋና ፈተና ይሆናል ተብሎ ከሚገመቱ ውስጥ ሀገሪቷ አሁን ያለችበትን የጸጥታ ሁኔታ ማሻሻልና አልሸባብን መጋፈጥ ዋነኛዎቹ ናቸው። በሶማሊያ ከፕረዚዳንቱ ቀጥሎ ትልቁን የመሪነት ሚና የሚጫወተውን ጠቅላይ ምኒስትር መምረጥም ከዋናዎቹ ፈተናዎች አንዱ እንደሚሆን ተገምቶ ነበር።

ጠቅላይ ምኒስትርመንግስታዊና ዲፕሎሚያሲያዊ የሆኑ ምንጮች እንደሚገልጹት የጠቅላይ ምኒስትሩ መመረጥ ባላፈት ሃያ ዓመታት የሶማሊያ አስተዳደር ውስጥ ትልቁ ውሳኔ ነው ተብሏል። የሶማሊያ ፖሊቲካ ተንታኙ አብዱልሃኪም አዪንቴ፣ የጠቅላይ ምኒስትርነት ስልጣን በሶማሊያ ዋነኛ የመንግስት ያላፊነት የሚወጣበት ነው ይላሉ፣

«የጠቅላይ ምኒስትርነት ቦታ ሶማሊያ ውስጥ ከፕሬዚዳንቱ ቀጥሎ በጣም አስፈላጊው ቦታ ነው። ለ28 ቀናት በላይ ፕሬዚዳንቱ አዲስ ጠቅላይ ምኒስቴር ለመምረጥ ሲያሰላስሉ ነበር። በመጨረሻም ለጠቅላይ ምኒስቴርነት ትክክለኛ ሰው ነው ብለው ያመኑበትን ለመሾም ወስነዋል። በጥቅሉ አስተዳዳራዊ ሥራዎችንና የመንግስትን ትላልቅ ኃላፊነቶችን በተግባር የሚወጣው ጠቅላይ ምኒስቴሩ ነው።»

Residents walk past the campaign billboard of Somalia's presidential candidate Hassan Sheikh Mohamud in Somalia's capital Mogadishu, September 9, 2012. Somalia's lawmakers voted overwhelmingly on Monday for Mohamud as the country's next president, with the streets of the capital erupting into celebratory gunfire, Reuters witnesses said. Two of the four candidates who made it to the second round of voting opted out, leaving the incumbent President Sheikh Sharif Ahmed and Mohamud.Picture taken September 9, 2012. REUTERS/Feisal Omar (SOMALIA - Tags: POLITICS ELECTIONS)

የሶማልያ ፕሬዚደንት ሀሰን ሸክ መሀመድ

ከትናንት በስቲያ በፕሬዚዳንቱ የተሾሙት አብዲ ፋራህ ሺርዶን የሲያድ ባሬ መንግስት መውደቁን ተከትሎ ሶማሊያን ትተው በመሸሽ ኬኒያ ውስጥ ቆይተዋል። እዚያም ውስጥ በውጭ ንግድ ዘርፍ ተሰማርተው ነበር። ጠቅላይ ምኒስትርከሶማሊያ ከመውጣታቸው በፊት እዚያው ሶማሊያ ኢኮኖሚክስ ያጠኑ አብዲ ፋራህ በተለይም ሶማሊያ ከተዘፈችበት ሙስና እንድትወጣ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ የሚል ተስፋ አይሏል። ግን አሁን ቅድሚያ ሊያገኝ የሚገባው ጉዳይ ሀገሪቷን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሲያበጣብጥ የቆየው የጎሳ ፖሊቲካን ማረጋጋትና ያገሪቷን ጸጥታ ማስጠበቅ ይሆናል። በንግድና ምጣነ ሐብቱ ዙሪያ ልምድ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስቴር የጸጥታ ጥያቄ አንገብጋቢ በሆነበት ሶማሊያ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸው የፖሊቲካ ተንታኙን አብዱልሃኪም አዪንቴ አላሳሰባቸውም። ይልቅ እርሱ የሚለው ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል ነው፣
«ፕሬዚዳንቱ ለዚህ ስራ እንደ ትክክለኛ ሰው ይመለከቷቸዋል። ነገር ግን በሀገሪቷና ለቦታው ትክክለኛ ስለመሆናቸው የተለያዩ ሰዎች የተለያየ ሐሳብ አላቸው። የሶማሊያን ቀውስ ማስተናገድ የማይችሉ ብቁ ያልሆኑና ችሎታ አልባ ሰው አርገው የሚወስዷቸው ሰዎች አሉ። ይህ የፕሬዞዳንቱ ውሳኔ ነው። እንዴት ሀገሪቱን እንደሚመሩ ጊዜ ሰጥተን ማየት አለብን። አሁን ቀድሜን እንዲህ ነው ብለን መናገር አንችልም።»
የሶማሊያ ፕሬዚዳንትም ሆነ አዲሱ ተመራጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ለፖሊቲካው ዓለም አዲስ በመሆናቸው የሚጋጥማቸው ፈተና ቀላል አይሆንም። በተለይም ሁለቱ ያገሪቷን ጸጥታ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ እቅድ ይዘው መጓዝ ግድ ይላቸዋል። ሶማሊያን ከአልሸባብ ፍራቻ ነጻ የማድረግና ክልላዊ አስተዳደሮችን ማጠናከርና ወደ የጋራ መድረክ ማምጣት እንዲሁም የሶማሊያን ጦር ማጠናከር ሁለቱን የሶማሊያ የበላይ መሪዎችን ከሚፈታተኗቸው ችግሮች ዋነኞቹ ናቸው። ባገሪቷ የተንሰራፋው ሙስናና የጎረቤት ሀገሮችን ጣልቃ ገቢነት መጋፈጥም ቀላል ስራ እንደማይሆን ይገመታል።
አብዲ ፋራህ ሺርዶን ባሳለፍነው ቅዳሜ ለሶማሊያ ጠቅላይ ምኒስትርነት ሲሾሙ ብቁ የሆነ ካቢኔ አቋቁመው የተሻለችዋን ሶማሊያ ለመፍጠር እንደሚተጉ ቃል ገብተዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ፣ አሻ ሃጂ ኤልሚ ከምትባል ታዋቂዋ የሶማሊያ የሰላም ተሟጋች ጋር በጋብቻ ተጣምረዋል። የአብዲ ፋራህ ሺርዶን ሹመት የሚጸድቀው በሶማሊያ የፈደራል ፓርላማ ነው።

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች