ከእስረኝነት ወደ ሀገር ፕሬዝደንትነት፤ አዲሱ የሴኔጋል መሪ
ቅዳሜ፣ መጋቢት 21 2016በሥልጣን ላይ የነበሩት የቀድሞው የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በተደጋጋሚ ምርጫውን ወደሌላ ጊዜ ለመግፋት ያደረጉት ሙከራ በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ሕግን የተከተለ ውሳኔ ውድቅ ከተደረገ በኋላ ሀገሪቱ ያልተጠበቀና መላውን ዓለም ያስደመመ ምርጫ አካሂዳ አሸናፊውን ይፋ ለማድረግ በቅታለች። በዚህ ምርጫ አሸንፈው ማኪ ሳል የሳሱለትን ፕሬዝደንታዊ ሥልጣን የተረከቡት ደግሞ የግብር መርማሪ የነበሩት የመንግሥት ሠራተኛና የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የ44 ዓመቱ ባሲሩ ደማ ፋይ መሆናቸው ይፋ ሆኗል። የዳካር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አማዲ ዲዮፍ ትናንት ማምሻውን የምርጫ ውጤቱን አረጋግጠዋል። «ባሲሩ ደማይ ፋይ፤ በትክክል እገልጻለሁ 54,28 በመቶ ድምጽ፤ 54,28 በመቶ።»
ከእስረኝነት ወደ ሀገር ፕሬዝደንትነት
ባሲሩ ደማይ ፋይ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ከሆኑት ፖለቲከኛ ኦስማን ሱንኮ ጋር የቅርብ አጋር ከመሆን አልፈው ለእስራት የተዳረጉትም በእሳቸው ምክንያት ነው። ሱንኮ በስም ማጥፋት እና ለአቅመ ሔዋን ያልደረሰች ልጅ በመድፈር ተከሰው ሲታሰሩ ፋይ ይህን በመቃወም በፌስቡክ ገጻቸው የጻፉት ለአንድ ዓመት በእስር እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። በእርግጥ ሱንኮ ከቀረበባቸው ያልደረሰች ልጅ መድፈር ክስ በፍርድ ቤት ነጻ መሆናቸው ተገልጿል። ሱንኮ እና ፋይ ከእስር በወጡ ከሁለት ሳምንታት ባነሰ ጊዜ ነው የሴኔጋል ምርጫ የተካሄደው። ሳንኩ በምርጫው ከመወዳደር ስለታገዱ ለእሳቸው ሲሉ የታሰሩት ፋይ በእሳቸው ምትክ እንዲወዳደሩ ድጋፋቸውን በመስጠት የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻውን በጋራ አጧጧፉ። እንደውም ድምጽ ለመስጠት የወጡት አብዛኞቹ ወጣቶች «የምመርጠው ሳንኩን ነው» ሲሉ እንደነበር ነው የተዘገበው። በእርግጥም ለሶንኩ የታለመው ድምጽ እስከ መታሰር ድረስ መስዋዕትነት የከፈሉላቸው የፋይን የምርጫ ኮሮጆ ሳይሞላው አልቀረም። እናም በምርጫው አብላጫውን የመራጭ ድምጽ ማግኘታቸው ይፋ ሆኗል። አሁን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሴኔጋልን በፕሬዝደንትነት ለመምራት እጅግም እውቅና ያልነበራቸው እስር ቤት የከረሙት ፖለቲከኛ ባሲሩ ዳማይ ፋይ እድሉን አግኝተዋል። የምርጫው ውጤት ከታወቀ በኋላም ፋይ ለሀገራቸውም ሆነ ውዝግብ ያጀበውን የሴኔጋልን ምርጫ በትኩረት ሲከታተል ለነበረው ሁሉ የሚከተለውን መልእክት አስተላለፉ።፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ከሆኑት ፖለቲከኛ ኦስማን ሱንኮ ጋር የቅርብ አጋር ከመሆን አልፈው ለእስራት የተዳረጉትም በእሳቸው ምክንያት ነው። ሱንኮ በስም ማጥፋት እና ለአቅመ ሔዋን ያልደረሰች ልጅ በመድፈር ተከሰው ሲታሰሩ ፋይ ይህን በመቃወም በፌስቡክ ገጻቸው የጻፉት ለአንድ ዓመት በእስር እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። በእርግጥ ሱንኮ ከቀረበባቸው ያልደረሰች ልጅ መድፈር ክስ በፍርድ ቤት ነጻ መሆናቸው ተገልጿል። ሱንኮ እና ፋይ ከእስር በወጡ ከሁለት ሳምንታት ባነሰ ጊዜ ነው የሴኔጋል ምርጫ የተካሄደው። ሳንኩ በምርጫው ከመወዳደር ስለታገዱ ለእሳቸው ሲሉ የታሰሩት ፋይ በእሳቸው ምትክ እንዲወዳደሩ ድጋፋቸውን በመስጠት የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻውን በጋራ አጧጧፉ። እንደውም ድምጽ ለመስጠት የወጡት አብዛኞቹ ወጣቶች «የምመርጠው ሳንኩን ነው» ሲሉ እንደነበር ነው የተዘገበው። በእርግጥም ለሶንኩ የታለመው ድምጽ እስከ መታሰር ድረስ መስዋዕትነት የከፈሉላቸው የፋይን የምርጫኮሮጆ ሳይሞላው አልቀረም። እናም በምርጫው አብላጫውን የመራጭ ድምጽ ማግኘታቸው ይፋ ሆኗል። አሁን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሴኔጋልን በፕሬዝደንትነት ለመምራት እጅግም እውቅና ያልነበራቸው እስር ቤት የከረሙት ፖለቲከኛ ባሲሩ ዳማይ ፋይ እድሉን አግኝተዋል። የምርጫው ውጤት ከታወቀ በኋላም ፋይ ለሀገራቸውም ሆነ ውዝግብ ያጀበውን የሴኔጋልን ምርጫ በትኩረት ሲከታተል ለነበረው ሁሉ የሚከተለውን መልእክት አስተላለፉ።
«የሴኔጋልን ባህል በማክበር ውጤቱ ይፋ ከመነገሩ አስቀድመው ላሳዩት ስነምግባር የእጩ ተፎካካሪዎችን አደንቃለሁ፤ የእነሱ የእንኳን ደስ ያለህ መልእክት ለታላቅነታቸው ድንቅ ማሳያ ነውና። ድክመቶችን በማረም እና አንዳንድ አሰራሮችን፤ ስልቶች በመቀየር ኤኮዋስን አዋህዶ በመመስረት ሂደት የታየውን ትብብር ለማጠናከር ለአፍሪቃ ወንድሞች እና እህቶቻችንም ጥሪዬን አቀርባለሁ። ለዓለም አቀፉ ማኅበርሰብ፣ ለሁለትዮሽና ለዘርፈ ብዙ ለአጋሮች ሴኔጋል ምንጊዜም ቁርጠኝነቷን እንደምታከብር መግለጽ እፈልጋለሁ። ሴኔጋል በመርህ፤ በአክብሮት እና በጋራ የልማት ትብብር ለተጎዳኛት ሁሉ ወዳጅ እና አስተማማኝ አጋር ሆና ትቀጥላለች።»
አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማን ናቸው?
ከፖለቲካ ይልቅ በልጅነቱ የእግር ኳስ ተጫዋች የሚያዘወትር እንዲሁም የስፔኑ ሪያል ማድሪድ ቀንደኛ ደጋፊና አድናቂ የነበረው ባሲሩ ደማይ ፋይ በእኩያ የልጅነት ጓደኞቹ የሚገለጸው እረጋ ባለው ሰብእናው ነው። ከ10 በላይ ልጆች በነበሩት ቤተሰብ ውስጥ ያደገው ፋይ ከእኩዮቹ ጋር ከመጫወት ባለፈ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ማንበብ ይወድ እንደነበር ነው በቅርብ የሚያውቁት የቤተሰብ አባላት እማኝነታቸውን የገለጹት። ፋይ ተወልደው ባደጉባት መንደር ወላጅ አባታቸው ከሀገር ሽማግሌዎች አንዱ ሲሆኑ በማኅበረሰቡ ውስጥ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ተሰሚነት ያተረፉ የ84 ዓመት አዛውንት ናቸው። አባታቸው ሳምባ ናዲጋኔ ፋይ ለሀገር መሪነት ስለተመረጠው ልጃቸው ሲናገሩም፤ «ታማኝ፣ ትሁት እና በገንዘብ የማይመራ እንዲሆን ስነግረው ኖሬያለሁ» ይላሉ። በምርጫው ዕለት ዋዜማ የእሳቸውን ምርቃትና ጸሎት ፍለጋ ወደቤታቸው ለመጣው የሀገራቸው መሪ ለሆነው ልጃቸው ያሳሰቡትንም እንዲህ ይገልጻሉ።
«አሁን የሴኔጋል ከባድ ኃላፊነትና ሀገሪቱን እንዲገነባ ተስፋ ያደረጉ ዜጎች ፍላጎት ትከሻው ላይ ማረፉን ነግሬዋለሁ። በልጅነቱ የሰጠነውን እሴት እንዳይጥል፤ ሁልጊዜም ለእውነት እንዲቆም እና የሴኔጋልን ሕዝብ ፍላጎት ለማሟላት የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግም ጠይቄዋለሁ።»
አሁን የያኔው እግር ኳስ አፍቃሪና ተጫዋች የሀገር መሪነትን ኃላፊነት ተረክበዋል። ያደጉባት መንደርና ቤተሰብ ለፍትህ የሚሟገትና የሚፋለም ለመሆኑ ማሳያም የሴኔጋል የቀድሞ ቅኝ ገዢ የፈረንሳይን ጣልቃ ገብነት አጥብቀው ከሚቃወሙ ተርታ በሴኔጋል ታሪክ ወጣቱ ፕሬዝደንት ባሲሩ ደማይ ፋይ ተሰልፈዋል። የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑት ፋይ ከምዕራባውያን ሠራሽ ሙሉ ሱፍ ልብሶች ይልቅ በሃይማኖታቸውም ሆነ በሴኔጋል ባህል ወደሚዘወተረው አለባበስ የሚያዘነብሉ፤ የሁለት ሚስቶች ባል ናቸው። ሴኔጋል ውስጥ ከአንድ በላይ ማግባት የተለመደ በመሆኑ እሳቸውም የሁለት ሚስቶች ባልነታቸውን በይፋ ነው የሚገልጹት። እንደውም በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ከሁለቱ ሚስቶቻቸው ጋር በየቦታው በመዘዋወር መታየታቸው የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ስቦ ነበር። ከመጀመሪያ ባለቤታቸው አራት ልጆችን ያፈሩት ፋይ አንድ ልጃቸውን በሚወዷቸውና እስከ እስር ድረስ በተሟገቱላቸው ኦስማን ሶንኮ ስም ኦስማን ብለው መሰየማቸውንም በቅርብ የሚያውቋጠው ይናገራሉ።
ሴኔጋል ለአፍሪቃ ሃገራት ተምሳሌት
በአፍሪቃ መሪዎች ዘንድ ባልተለመደ ሁኔታ አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዝደንት ያላቸውን የግል ሀብትና ንብረት ገና ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸው ተሰምቷል። የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩት ፋይ ዳካር ውስጥ የሠሩትን ቤት እንዲሁም በትውልድ መንደራቸው የሚያለሙትን የእርሻ መሬት በግላቸው ያፈሩት ጥሪት መሆኑት ዐሳውቀዋል። ቤት የሠሩት የሴኔጋል መንግሥት ለተቀጣሪ ሠራተኞቹ መሬት በሚያከፋፍልበት መርሃግብር አማካኝነት ነው። በእርሻ መሬታቸውም ለገበያ የሚቀርቡ አትክልት እና ፍራፍሬ እንደሚመረት፤ እሳቸውም ቢሆኑ የመንግሥት ሥራቸውን በመተው ወደ ፖለቲከኝነትና ወደ ግብርናው ይበልጥ ለማተኮር ያስቡ እንደነበር ነው የተነገረው።
19 እጩዎች በተሳተፉበት የሴኔጋል ምርጫ በፖለቲካው መድረክ እምብዛም እውቅና ያልነበራቸው ፋይ ማሸነፋቸውን በቀድሞው ፕሬዝደንት የሚደገፉት ተፎካካሪያቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ባ የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክት በማስተላለፍ ነው ያረጋገጡት። ይፋ በተነገረው መሠረት ፋይ 54,28 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ ባ ያገኙት ደግሞ 35,47 በመቶ ነው። የአፍሪቃ ሕብረት ለፋይ እና ለሴኔጋል የደስታ መልእክቱን አስተላልፏል። ፋይ ማክሰኞ ዕለት በይፋ ከማኪ ሳል ፕሬዝደንታዊ ሥልጣኑን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ