አዲሱ የሊቢያ ምክር ቤት ሥልጣን መረከቡ | አፍሪቃ | DW | 09.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አዲሱ የሊቢያ ምክር ቤት ሥልጣን መረከቡ

በሊቢያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት በትናንቱ ዕለት ሥልጣኑን ከአንድ ወር በፊት በነፃ ለተመረጠው አዲሱ ምክር ቤት አስረከበ። 200እንደራሴዎች ያሉት ምክር ቤት የቀድሞው መሪ ሞአመር ኧል ጋዳፊ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ሀገሪቱን ሲመራ የቆየውን የሽግግሩን ምክር ቤት ተክቶዋል።

የሊቢያ የሽግግር ምክር ቤት ለአዲሱ አጠቃላይ ብሄራዊ ምክር ቤት ስልጣኑን ትናንት ማምሻዉን በይፋ አሸጋገረ። ባለፈዉ በተካሄደዉ ብሄራዊ ምርጫ ለተመረጠዉ አጠቃላይ ብሄራዊ ምክር ቤት ስልጣኑን ያስረከቡት የሽግግር ምክር ቤቱ የበላይ ሙስጠፋ አብደል ጃሊል፤ ዕለቱን ታሪካዊ ብለዉታል። የምክር ቤቱ 200 አባላት የስልጣን ሽግግሩ ከመደረጉ ሰዓታት አስቀድሞ ቃለመሀላ ፈፅመዋል። በሙስሊሞች የሮመዳን ፆም ምክንያት ማምሻዉን የተከናወነዉ የስልጣን ሽግግር ሂደትም ከ40ዓመቱ የኮሎኔል ሞሐመድ ኤል ጋዳፊ ከስልጣን መባረር በኋላ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተምሳሌት ተብሏል።

libyen dschalil jalil übergangsrat

ሙስጠፋ አብደል ጃሊል

ምክር ቤቱ መንግስት የሚመሠርት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሰይማል። ሊቢያ ሙሉ ምክር ቤታዊ ምርጫ እንድታካሂድ የሚያስችል ህግና መመሪያም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ አባላት ከግል እጩዎችና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የተዉጣጡ መሆናቸዉ ተዘግቧል።
በመዲናይቱ ትሪፖሊ የተከናወነው የርክክብ ሥነ ሥርዓት በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ የተላለፈበት የመጀመሪያው ነው። ስለሰላማዊው የሥልጣን ርክክብ ቀደም ሲል ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት የጄዳውን ወኪላችን ነቢዩ ሲራክን አነጋግሬ ነበር። በመጀመሪያ የጠየቅሁት የአዲሱ የሊቢያ ምክር ቤት የወደፊት ተግባር ምን ሊሆን እንደሚችልና የሊቢያስ ሕዝብ ከአዲሱ ምክር ቤት ምን እንደሚጠብቅ ነበር።

ሸዋዬ ለገሠ/ ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች