አውሮፕላን ሠርቶ የመብረር ሕልም | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 23.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

አውሮፕላን ሠርቶ የመብረር ሕልም

K-570 ሲል ስያሜ የሰጣትን አውሮፕላኑን ኢትዮጵያ ውስጥ ገጣጥሞ የሠራው ከመርካቶ የተለያዩ አካባቢ ባሰባሰባቸው ቁሶች እንደሆነ ይናገራል። በሙያው የጤና መኮንን ነው። ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተምሮ በዲግሪ የተመረቀውም በጤና መኮንንነት ዘርፍ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:26
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:26 ደቂቃ

አውሮፕላን ሠርቶ የመብረር ሕልም

በሁለተኛ ሙከራዬ K-570 አውሮፕላኔን አብርሬ ባሳረፍኩበት ቅጽበት እጮኛዬን አገባለሁ ሲልም ዕቅዱን አጫውቶናል። ሰኔ ወር ላይ ያከናወነው የመጀመሪያ ይፋዊ የበረራ ሙከራው ውጤትን ተከትሎ ምን ለማድረግ አስቧል።

አውሮፕላን ሠርቶ ማብረር እጅግ ውስብስብ የስነ-ቴክኒክ ዕውቀት ይጠይቃል። ኢትዮጵያዊው አስመላሽ ዘፈሩ የመጀመሪያ ይፋዊ የበረራ ሙከራውን ያደረገው ከወራት በፊት ነበር። ሙከራው ምን ይመስል ነበር?

በዓለም የአውሮፕላን በረራ ታሪክ የመጀመሪያውን ፈር የቀደዱት አሜሪካውያኑ ወንድማማቾች፤ ዊልቡር እና ኦርቪለ ራይት ናቸው። ወንድማማቾቹ የመጀመሪያ ሙከራቸውን ካከናወኑ 112 ዓመታት አልፏል። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ታህሳስ 17 ቀን 1903 ዓም ኦርቪለ ሰሜን ካሮሊና ውስጥ ከመሬት 6 ሜትር ከፍ በማለት ለ12 ሰከንዶች መብረሩ በታሪክ ድርሳናት ሰፍሮ ይገኛል። በዛው ዕለት ወንድሙ ዊልቡር 59 ሰከንዶች የፈጁ ሦስት ተከታታይ የበረራ ሙከራዎችን አድርጎ ነበር። አሜሪካውያኑ ወንድማማቾች የነበራቸው ሣይንሳዊ ዕውቀት ጥቂት እንደነበር በታሪክ ይጠቀሳል።

ኢትዮጵያዊው አስመላሽ ዘፈሩም የበረራ ዕውቀቱን የገበየው ከኢንተርኔ ነው። በበረራ ሣይንስ ትልቁ ነጥብ ያለው ክንፍ ላይ እንደሆነ የሚገልጠው አስመላሽ ከባዱ ነገር አውሮፕላንን ማስነሳት ሳይሆን ማሳረፍ ነው ይላል። የመጀመሪያ የበረራ ሙከራው የአየር መቅዘፊያዋ ተገንጥሎ ሳይሳካ ቢቀርም ወደፊት ግን የገጣጠማትን አውሮፕላን አብርሮ ለማሳረፍ እርግጠኛ እንደሆነ ይናገራል። በእርግጥ ታዲያ እንደለማጅ አውሮፕላን አስነስቶ ለማሳረፍ መሞከር አደገኛ ነው ይላል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማጫወቻውን ይጫኑ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic