1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አውሮፓ ለመግባት የሚደረገ አደገኛ የስደት ጉዞ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2001

በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከሚሞክሩት እና መሰል አደጋ ከሚደርስባቸው አፍሪቃውያን ውስጥ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንም ይገኙበታል ።

https://p.dw.com/p/HP8u
ነፍሳቸውን የሸጡት ስደተኞች በባህር ላይ
ነፍሳቸውን የሸጡት ስደተኞች በባህር ላይምስል AP

በዚህ ዓይነቱ ጉዞ ሜዴትራኒያን ባህር ውስጥ የሰጠሙ ፣ የባህሩ ጉዞ አልሳካ ብሏቸው በሊቢያ የሚንከራተቱ ፣ ከዚያም በባሰ ሁኔታ በሱዳንና በሊቢያ ዕስርቤቶች እንዲሁም በማልታ የስደተኞች ማጎሪያ የሚማቅቁ በርካታ ናቸው ። የተሻለ ኑሮ እና ህይወት ፍለጋ ከሞቀ ቤታቸው ፤ ከነሙሉ አካላቸው ወጥተው ለተለያዩ የጤና ችግሮች የተዳረጉም ጥቂት አይደሉም ። አንዳንዶች ደግሞ መከራውንም ችግሩንም ተቋቁመው እንደ ዕድል ማለት ይቻላል አውሮፓ ይደርሳሉ ። ከነዚህ ውስጥ ከዛሬ ሶሶት ዓመት በፊት ከአገራቸው ወጥተው ከሁለት ዓመት ስቃይና መከራ በኃላ አውሮፓ የገቡት አራት የአዲስ አበባ ልጆች ይጠቀሳሉ ። ወጣቶች ናቸው ፤ ከጓደኛቸው የሰሙትን አምነው ነበር ገንዘባቸውን ቋጥረው ከአዲስ አበባ የተንቀሳቀሱት ።

(ክፍል አንድ)

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የ.ኋላ