አውሮፓና ፀረ- አይ ኤሱ ትግል | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አውሮፓና ፀረ- አይ ኤሱ ትግል

ምዕራቡ ዓለም ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ በሚጠራው በምህፃሩ IS በተባለው ቡድን ላይ በህብረት የሚያካሂደውን ዘመቻ ቀጥሏል ።ከሦስት ሳምንት በፊት ከደረሰው የፈረንሳይ የሽብር ጥቃት በኋላ በተለይ የአውሮፓ ሃገራት በፍልሚያው ለመሠማራት ተነስተዋል ። ፀረ አይሱ ትግል ደግሞ አሉታዊ ውጤት ያመጣል የሚል ስጋት አሳድሯል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:30
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
09:30 ደቂቃ

አውሮፓና ፀረ- አይ ኤሱ ትግል

ከዛሬ ሦስት ሳምንቱ የፓሪሱ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ በአውሮፓ ለፀረ ሽብሩ እርምጃ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷል ። ፈረንሳይ ጀርመን ብሪታንያና ሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ሶሪያ ውስጥ ውጊያ የሚያካሂደውን IS ን ለመታገል ታጥቀው ተነስተዋል ። ዩናይትድ ስቴትስ በምትመራው ፀረ-IS ህብረት ፈረንሳይና ብሪታኒያ ፣ እንዲሁም የአረብ ሃገራት በሶሪያ የIS በሚባሉ ይዞታዎች ላይ የሚያካሂዱት የአየር ድብደባ ቀጥሏል ።ሩስያ በፊናዋ IS እየወጋች ነው ። የጀርመን መንግሥትም በሶሪያው ውጊያ ለመካፈል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ወስኗል ።የጀርመንየሕዝብእንደራሴዎችምክር ቤትቡንደስታግ ባለፈው አርብ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረትራሱን «እስላማዊመንግሥት» ብሎ የሚጠራውንአሸባሪቡድንለመውጋት የጀርመን መንግሥት 6 መረጃሰብሳቢ «ቶርኔዶ» የጦርአውሮፕላኖችንእናአንድ ነዳጅ አስተላላፊ የጦር አውሮፕላን እንዲሁም 1,200 ወታደሮችወደ ሶሪያ ያዘምታል ።በ445 የድጋፍ በ146 ተቃውሞ እና በ7 ድምፀ ተአቅቦ ባለፈው በዚህ እቅድ ከመረጃሰብሳቢዎቹ አዉሮፕላኖች ሁለቱ ወደ ቱርክ እንደሚላኩ ተነግሯል ። እስከ ጎርጎሮሳዊው 2016 መጨረሻ ድረስ ይዘልቃል የተባለውና 134 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም 142 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣ የተነገረው ጥምሩ መንግሥት ሥራ ላይ የሚያውለው ይህ ወታደራዊ ተልዕኮ ብዙ አወዛግቧል። የእቅዱ ተቃዋሚዎች ከጦር እርምጃ ይልቅ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ይፈለግ የሚል ሃሳብ ሲያቀርቡ ነበር ። ሌሎች ደግሞ ጊዜ ተወስዶ ሳይመከርበት የተላለፈ የጥድፊያ ውሳኔ ነው ሲሉ አጣጥለውታል ። በጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የእህትማማቾቹ የክርስቲያን ዴሞክራት ህብረት በምህፃሩፃሩ CDU እና ና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት በምህፃሩ CSU ፓርቲዎች ስራ አስኪያጅ ኖርቤርት ረተገን በሶሪያ የጀርመን ወታደራዊ ተልዕኮን አስፈላጊነት ለምክር

ቤቱ እንዲህ ሲሉ ነበር ያስረዱት ።

«ክቡራትና ክቡራን ፣በሶሪያ በኢራቅ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ካለ ምዕራቡ ዓለም ወታደራዊ ስምሬት ዲፕሎማሲያዊው እርምጃ ምንም ውጤት አያመጣም ።»

የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና የመከላከያ ሚኒስትር ኤርዙላ ፎን ዴር ላዬን ለፈረንሳይ ቃላቸውን በሰጡት መሠረት የገቡበት ዘመቻ ISን ከመታገሉ ጋር ሌሎች ዓላማዎችንም ያቀፈ እንደሚሆን መከላከያ ሚኒስትር ፎን ዴር ላየን ገልፀዋል ።

«ይህ ተልዕኮ ፣ይህ ስምሬት በትልቅ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ የታቀፈ ነው ።በማናቸውም ደረጃ IS ን መውጋት ማለትም በወታደራዊ ፖለቲካዊ በኤኮኖሚያዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ትግልንም ይጨምራል ።»

የጀርመን ጥምር መንግሥት የሶሪያውን ተልዕኮ አስፈላጊነት በዚህ መልኩ ቢያስረዳም ተቃዋሚዎቹ አረንጓዴዎቹና የግራዎቹ ፓርቲዎች ሃሳቡን አልተቀበሉትም ። ተልዕኮው ተቃራኒ ውጤት ነው የሚያስገኘው የሚሉት ተቃዋሚዎች ስምሪቱ ዓላማውን ሊያሳካ አይችልም በጀርመን የሽብር ጥቃት ስጋት እንዲጨምር ያደርጋል ሲሉ ይከራከራሉ ። ይህን አፅንኦት ሰጥተው ከተናገሩት መካከል በጀርመን ምክር ቤት የግራዎቹ ፓርቲ ተጠሪ ሳራ ቫገንክኔሽት ይገኙበታል ።

«ጦርነት ሁሉን ነገር ይበልጥ ያባብሰዋል ።በዚህ መንገድ ISን መዋጋት አይችሉም ።በዚህ ተልዕኮ ይበልጥ ያጠናክሩታል ።»

የጀርመን የሶሪያ ዘመቻ ይህን መሰል ተቃውሞ ቢነሳበትም የዘመቻው ዝግጅት ተጠናቋል ።ህዳር 3 2008 ዓም የደረሰው የፓሪሱ የሽብር ጥቃት ድንጋጤና ቁጭትን አስከትሉ ምዕራባውያን በሶሪያ ለፀረ ሽብሩ ዘመቻ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጡ አድርጓል ። ይሁንና ከ14 ዓመት በፊት በኒውዮርኮቹ መንታ ህንፃዎች ላይ የሽብር ጥቃቶች ከተፈጸሙ በኋላ በአፍጋኒስታንና

በኢራቅ የተካሄዱት ዓለም ዓቀፍ ዘመቻዎች እንዲሁም የሊቢያው ጦርነት ያስገኙት አሉታዊ ውጤቶች በሶሪያው ዘመቻም እንዳይደገም ማስጋቱ አልቀረም ። ዩናይትድ ስቴትስና አውሮፓ በIS ላይ በከፈቱት ዘመቻ ካለፈው ስህተታቸው ምን ትምህርት ይወስዱ ይሆን ?በርካቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው ። በጀርመኑ የድዩስበርግ -ኤሰን ዩኒቨርስቲ የልማትና የሰላም ጥናት ተቋም ባልደረባ ዮኽን ሂፕለር ከከዚህ ቀደሞቹ እርምጃዎች በመነሳት የምዕራባውያን ጣልቃገብነት መጀመሪያው እንጂ መጨረሻው እንደማያምር ልናስተውል ይገባል ይላሉ

«በአፍጋኒስታን በኢራቅ እና በሊቢያ የተካሄዱት የተለያዩ ጣልቃ ገብነቶች በአጠቃላይ ቀጥተኛ ወታደራዊ ዓላማቸውን ወዲያውኑ አሳክተዋል ። በአፍጋኒስታን የታሊባንን ውድቀት፣ በኢራቅ የሳዳም ሁሴን እንዲሁም በሊቢያ የሞአመር ጋዳፊ ከሥልጣን መውረድን አሳክተዋል ። ሆኖም ይህ ጥሩ የመሰለው ውጤት ግን በኋላ በተቃራኒው ተቀልብሷል ።»

ሂፕለር እንዳሉት ኢራቅ አሁን የአሸባሪዎች መፈልፈያ ሆናለች ። በኢራቅ የተፈጠረው የኃይል ክፍተት በሲሪያ የተከተተለው አለመረጋጋት IS ፈጥሯል ።IS አሁን ሊቢያንም ቤቱ አድርጓል ። ካለፈው ወሩ የፓሪስ ጥቃት ወዲህ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በአጠቃልi aneዲሁም አውሮፓ ና ዩናይትድ ስቴትስ በተለይ በቅርብ ዓመታት የሰሯቸውን ስህተቶች እየደገሙ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እንዳሉ ምሁራን ይናገራሉ ። ሚሻኤል ልዩደር የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና የእስልምና ጉዳዮች አዋቂ ናቸው ። ልዩደር ምዕራባውያን ከቀድሞው ስህተታቸው ሊማሩ ይገባል ሲሉ ያሳስባሉ ።ሆኖም በርሳቸው አባባል ከልምድም እንደሚታወቀው ይህ ሲደረግ አይታይም ። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ስህተትን የማረም ፍላጎት መጥፋት ነው እንደ ልዩደር ። በርሳቸው አስተያየት በአሁኑ ጊዜ IS ፣ምዕራቡ ዓለም ርሱ በሚፈልገው የጦርነት ስልት ውስጥ እንዲገባ እየገፋው ነው ። ይህ ደግሞ የታሰበለትን ዓላማ አያሳካም ።

«የፖለቲካ መሪዎች በግልፅ እንደሚታየው ከዚህ ቀደም ከተሰሩት ስህተቶች ፈጽሞ መማር አይፈልጉም ። የምዕራባውያን ሃገራት ጣልቃ ገብነት ለሙስሊሙ ዓለም መረጋጋት ድጋፍ ማድረግ አለመቻሉን ይልቁንም በተቃራኒው በሚገባ የሚሠራ ማዕከላዊ መንግሥት የሌላቸው ሃገራት እንዲሆኑ ማድረጉን ከግምት ሲያስገቡ አልታየም ።ይህም ውጤታማ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም IS ምዕራቡ ዓለም አሸናፊ ሊሆን የማይችልበትን የእግረኛ ጦር እንዲያሰልፍ የሚያስገድድ ግልፅ ስልት እየተከተለ ነው ።መደበኛ ጦር መቼም ቢሆን ደፈጣ ተዋጊዎችን አሸንፎ አያውቅም ።»

ምንም እንኳን IS ግልፅ በሆነ ስልት እየተመራ ቢሆንም ሚሻኤል ልዩደር እንዳሉት የምዕራቡ ዓለም መሪዎች ደግሞ በርሱ ወጥመድ ውስጥ እየወደቁ ነው ።በርሳቸው አባባል መሆን ያለበት ዓለም ዓቀፍ ኃይሎች IS የተፅእኖ አድማሱን እንዳያሰፋ መከላከል ነው ። የእስካሁኑ አየር ድብደባው ደግሞ ከዚህ ዓላማ አብዛኛውን አሳክቷል እንደ ልዩደር ። ፈረንሳይ በሶሪያና ና በኢራቅ የአየር ጥቃቱን አጠናክራለች ።የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ IS በወታደራዊ እርምጃ ለማሸነፍ ነው የሚፈልጉት ለዚህ ዓላማቸው ከሞስኮ እስከ ዋሽንግተን ጠንካራ ህብረት የመፍጠር ዘመቻቸውን አጠናክረዋል ። ይህንኑ ጥሪአቸውንም የብሪታኒያና የጀርመን መንግሥታት ተቀብለዋል ። የበርሊኑ ዓለም ኦቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ተቋም ባልደረባ ቮልፍጋንግ ሪሽተር ይህን መሰሉ እርምጃ ብቻውን የትም አያደርስም ይላሉ ። ከዚያ ይልቅ በዚህ ዘመቻ ጦርነት በሚካሄድባቸው ሃገራት የሚገኙ ጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎችንም ሆነ ቡድኖች ከጎን ማሰለፍ እንደሚጠቅም ያስረዳሉ ።

«"ከIS ጋር በሚካሄደው ትግልበሶሪያና በኢራቅ ዋነኛ የሚባሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማካተት አስፈላጊ ነው ።ከዚህ በተጨማሪም በውጭ ኃይሎች ጥቅም ተፅእኖ ከሚደረግባቸው መንግሥታት ይልቅ IS ን የሚወጉ ሌሎች ለዘብተኛ ሱኒ መራሽ አማራጭ ቡድኖች ያስፈልጋሉ ። »

አሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የሚመራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቡድን በሶሪያ የሰላም ውል ላይ እንዲደረስ እየጣረ ነው ። ባለፈው ህዳር መጀመሪያ ላይ በሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አልአሳድና በለዘብተኛዎቹ አምፅያን መካከል ቭየና ኦስትሪያ ውስጥ ስምምነት ላይ ተደርሷል ።በመጪው የጎርጎሮሳውያኑ 2016 ዓመተ ምህረት አጋማሽ የቀድሞው ን አገዛዝና የተቃዋሚ ኃይሎችን ያካተተ የሽግግር መንግሥት የመ,ሥረት እቅድ አለ ።እንደ እቅዱ ከ18 ወራት በኋላም በሶሪያ ምርጫ ይካሄዳል ። በዚህ ምርጫም በዓለም ዙሪያ የተበተኑ ሶርያውያን ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ይህ ደግሞ IS ን በመዋጋቱ ሂደት አንድ ትክክለኛ አቅጣጫ የያዘ እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic