አውሮጳ እና የአፍሪቃ ፖሊሲዋ | አፍሪቃ | DW | 22.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አውሮጳ እና የአፍሪቃ ፖሊሲዋ

የአወሮጳ ህብረት ከአፍሪቃ ጋ በብራስልስ ጉባዔ ሊያደርግ ጥቂት ጊዜ በቀረበት ባሁኑ ጊዜ የጀርመን መንግሥት ለአፍሪቃ ህብረት ተጨማሪ ፊናንስ ርዳታ ለመስጠት ቃል ገባ። እርግጥ ፡ አፍሪቃውያን ለችግሮቻቸው ራሳቸው መፍትሔ ለማፈላለግ ይሻሉ፡ ያም ቢሆን ግን፡ ጀርመን ከጎናቸው መቆሟን የሀገሪቱ የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ

default

ሙለር ትናንት በፌዴራዊው ምክር ቤት በተካሄደ ክርክር ወቅት አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት፡ አፍሪቃውያን በአህጉራቸው ለሚያካሂዱዋቸው የሰላም ተልዕኮዎች እና ለአፍሪቃ የፀጥታ መዋቅር ማስፋፊያ አውሮጳውያን መንግሥታት የሚሰጡት የገንዘብ ርዳታ ወደ ዘጠኝ መቶ ሚልዮን ዩሮ ከፍ ይላል።

በአወሮጳ ህብረት እና በአፍሪቃ መካከል ለአራተኛ ጊዜ የተዘጋጀው ጉባዔ እአአ የፊታችን ሚያዝያ መጀመሪያ ላይ በብራስልሰ ይካሄዳል።

ወደ ሰማንያ የሚጠጉ ርዕሳነ ብሔር እና መራሕያነ መንግሥት የሚሳተፉበት ይኸወ ጉባዔ የሕዝብን ችሎታ ለመገንባት፡ ብልፅግናን እና ሰላምን ለማጠናከር የሚረዳ ኢንቬስትመንት » የሚል ርዕስ ይዞ ተነስቶዋል። የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከትናንት በስቲያ በምክር ቤት ባሰሙት ንግግራቸው ይኸወው ጉባዔ ከአፍሪቃ ጋ ዘላቂ እና አስተማማኝ የጋራ ትብብር እንዲፈጠር ጠንካራ ፍላጎት መኖሩን ግልጹን መልዕክት ማስተላለፍ እንዳለበት ነበር ያስታውቁት። የአፍሪቃ ህብረት የአፍሪቃ ህብረት ን እና ሌሎች ያካባቢ ድርጅቶችን ለማጠናከር እና ራሱም ባካባቢዎቹ ኃላፊነት በመውሰድ ትልቅ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚችል ጀርመናዊትዋ መሪ ገልጸዋል። አስተማማኝ አፍሪቃውያን አጋሮችን አፍሪቃውያን ራሳቸውን ሊረዱ የሚችሉበትን ርዳታ ማቅረብ ይችሉ እና የፀጥታውን ጥበቃም ራሳቸው ያካሂዱ ዘንድ አስፍላጊው ትብብር ሊደረግላቸው፡ ማለትም፡ ምክር፡ ሥልጠና እና ትጥቅ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ ሜርክል አስረድተዋል።

በዚህም ረገድ ጀርመን ለአፍሪቃ ትክክለኛ አጋር መሆኗን የልማት ትብብር ሚንስትር ሙለር አስታውቀዋል። ጀርመን በመሠረተ ልማቱ ግንባታ፡ እንዲሁም፡ ትምህርት እና ሀኪም ቤቶችን በመገንባቱ ተግባር የበኩሏን እያደረገች ትገኛለች።

የጀርመን መንግሥት ካለፉት በርካታ ወራት ወዲህ የርስ በርስ ጦርነት የሚካሄድባትን ማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክን የልማት ትብብሩ ማዕከል ለማድረግ እና አስቸኳዩን ርዳታ ለማቅረብ ወስኖዋል። ከፈረንሳይ ጋ በመሆን ያስተዳደሩን እና የአመጋገብ መዋቅሩን ዘረፍ ለማሰፋፋት ዕቅድ መያዛን ሙለር ገልጸዋል።

ከየሁለቱ አፍሪቃዊ አንዱ ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆነባት አፍሪቃ ለጀርመን እና ለአውሮጳ ግዙፍ የኢቬስትመንት እና የአጋርነት ዕድል የከፈተች አህጉር ናት። ከአፍሪቃ ጋ የሚደረግ ማንኛውም አጋርነት አህጉሩን እንደ እኩል የሚመለከት መሆን እንደሚገባው፡ ማለትም፡ ፍትሓዊ የንግድ ደንቦችን የያዘ ጀርመናዊቷ የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ፖለቲከኛ እና የልማቱ ትብብር ኮሚቴ አባል ቤርብል ኮፍለር አሳስበዋል። የአወሮጳ ገበያዎች ለአፍሪቃውያኑ ምርቶችም ክፍት ሊሆኑ ይገባል። አፍሪቃውያት ሀገራት የኤኮኖሚ ዘርፋቸው ስጋት ላይ እንዳይእወድቅ የሰጉት የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር አፍሪቃውያኑ ገበያዎቻቸውን በጣም እንዳይከፍቱ አስጠንቅቀዋል።

አውሮጳ ወደሀገራተዋ ለሚመጡ ስደተኞች ተገቢወን ስብዕና የተመላበት አቀባበል እንድታድርግ የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ፖለቲከኛ ኡቨ ኬከሪትሰ ተማፅነዋል። የአውሮጳ ህብረት በአፍሪቃ ግብር ሶዶማወያን እንደ ወንጀለኛ በሚታዩበት አሰራር አንፃር አቋም እንዲይዝ ኬከሪትሰ አክልው ጠይቀዋል።

የጀርመን የውጭ ጉዳየ ሚንንስትር ፍራንክ ቫልትር ሽታይንማየር በአፍሪቃ የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ነገ ማታ ወደዚኢኣው ይጓዛሉ። በዚሁ ጉዟቸው በመጀመሪያ ኢትዮጵያን፡ ቀጥለው ታንዛንያን እና አንጎላን ይጎብኛሉ። ሦስቱ ሀገራት በጀርመን የልማት ትብብር ፖለቲካ ላይ ትልቅ ትኩረት ያረፈባቸው ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የልዑካን ቡድን በሦስቱ ሀገራት ከመንግሥት ተወካዮች፡ ከተቃዋሚ ቡድኖች እና ከሲቭሉ ማህበረሰብም ጋ፡ እንዲሁም፡ በአዲስ አበባ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ተገናኝተው ሀሳብ ይለዋወጣል።

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic