አዉቶሞቢሎችና የሚያስከትሉት ብክለት | ጤና እና አካባቢ | DW | 04.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

አዉቶሞቢሎችና የሚያስከትሉት ብክለት

በጀርመን የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ተቆርቋሪዎች የአገሪቱ ፖለቲከኞች የሚያሽከረክሯቸዉ አዉቶሞቢሎች ምን ያህል በከባቢ አየር ላይ ጉዳት የማያስከትሉ እንደሆኑ ሲከታተሉ እና ሲታዘቡ ቆይተዋል።

default

...አቤት የCO2 ብዛት...

በቅርቡ የወጣ መረጃ የአገሪቱ ግንባር ቀደም ፖለቲከኞች አርአያ ለመሆን በያለበት የሚያሽከረክሩት በተፈጥሮ ላይ ጉዳት የማያስከትል እንደሆነ አመልክቷል። የእነሱ አርአያነት እንዳለሆኖ ምን ያህሉ ጀርመናዊ ምሳሌነታቸዉን ወስደዉላቸዋል? የሚለዉ ግን ማነጋገሩ አልቀረም። ምን ያህሉስ ዜጋ የአየር ንብረት መለወጥ ያሳስበዋል፤ ምን ያህልስ የበኩሉን ለማድረግ ይጥራል? የመጀመሪያዉ አዉቶሞቢል መገኛ የሆነችዉ ጀርመን፤ ምንም እንኳን ዜጎቿ ለመኪና ለየት ያለ ፍቅር እንዳላቸዉ ቢነገርም፤ በአካባቢ ተፈጥሮ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ጉዳት ከዚህ አንፃር ለመቀነስ እየሞከረች ይሆን?

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic