አዉሮጳ ዉስጥ የሚገደሉና ደብዛቸዉ የሚጣፋ ጋዜጠኞች ጉዳይ  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.10.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

አዉሮጳ ዉስጥ የሚገደሉና ደብዛቸዉ የሚጣፋ ጋዜጠኞች ጉዳይ 

የአንዲት ወጣት ቡልጋርያዊት የምርመራ ጋዜጠኛ ግድያ ጋዜጠኞችን ብቻ ሳይሆን ፤ የዴሞክራሲና የነፃ ፕሬስ አቀንቃኞችን ሁሉ በከፍተኛ ደረጃ አሳዝኖአል አስቆጥቶአልም። ወጣትዋ የምርመራ ጋዜጠኛ ቪክቶርያ ማሪኖቫ ተገድላ የተገኘችዉ በሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል በምትገኘዉ «ሩሴ» በተሰኘች ከተማ ነዉ።

 ጋዜጠኛዋ በምትሰራበት ቴሌቭዥን ከአዉሮጳ ኅብረት በተገኘ ገንዘብ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን የአፈፃፀም ጉድለት የሚመለከት ዘገባ ከአቀረበች በኋላ መሆኑ ግድያዉን ከስራዋ ጋር አያይዞታል።  በአዉሮጳ በተለይ ሙስናን በሚያጋልጡ ጋዜጠኞች ላይ አልፎ አልፎ ግድያ ይፈፀማል። ከአንድ ዓመት በፊት በፓናማዉ የሙስና ቅሌት «የታክስ ማጭበርበር» ጉዳይ ላይ ክትትል ታደርግ የነበረች የማልታ ጋዜጠኛ የነበረችበት ተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦንብ መገደልዋ የሚታወስ ነዉ። በሌላ በኩል ቱርክ ዉስጥ ደብዛቸዉ የጠፋዉ የሳዉዲአረብያ ጋዜጠኛም ጉዳይ የሰሞንኛ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ። ጋዜጠኛዉ በሳዉዲ አረብያ ትችት የሚያቀርብ ጋዜጠኛ ነበር። ዝርዝር ዘገባዉን የብረስልሱ ወኪላችን ልኮልናል። 


ገበያዉ ንጉሴ 


አዜብ ታደሰ 
አርያም ተክሌ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች