አዉሮጳ በብራስልስ ሽብር ማግሥት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አዉሮጳ በብራስልስ ሽብር ማግሥት

የቤልጅግ ሕዝብ ትናንት በሐገሪቱን ርዕሠ-ከተማ ብራስልስ በደረሰዉ የአሸባሪዎች ጥቃት የተገደሉ ወገኖቻቸዉን ዛሬ አስበዉ ዋሉ። የቤልጂግ መንግሥት በመላዉ ሐገሪቱ የሚፀና የሰወስት ቀን ብሔራዊ ሐዘን አዉጇል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:01
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:01 ደቂቃ

አዉሮጳ በብራስልስ ሽብር ማግሥት I

ትናንት ብብራስልስ አዉሮፕላን ማረፊያ እና በአንድ የምድር ዉስጥ ባቡር ጣቢያ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ ሰላሳ-አንድ ሰዎች ተገድለዋል። ከ250 በላይ ቆስለዋል ። ቦምቡን ካፈነዱት መካከል ሁለቱ በፍንዳታዉ ሲሞቱ ሰወስተኛዉ አሁንም እንደተሰወረ ነዉ። የአዉሮጳ ከተሞች በተደጋጋሚ በአሸባሪዎች መጠቃታቸዉ ዳግም የመነጋገሪያ ርዕሥ ሆኗል።

የቤልጅግዋ ርዕሰ-ከተማ ብራስልስ ትናንት በአሸባሪዎች ከተጠቃኝ ወዲሕ እዚያዉ ቤልጂግ እና በአጎራባቾችዋ ሐገራት የሚደረገዉ የፀጥታ ጥበቃ እና ቁጥጥር ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ።

ከፍተኛ ቁጥጥር ከሚደረግባቸዉ ሐገራት አንዷ ጀርመን ናት። የጀርመን ፀጥታ አስከባሪዎች በተለይ ሐገሪቱን ከቤልጂግ፤ ከፈረንሳይ፤ ከኔዘርላንድስ እና ሉክስምቡርግ ጋር የሚያዋስኑ ድንበሮችን በጥብቅ እየፈተቆጣጠሩ ነዉ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደታዘበዉ ደግሞ አዉሮፕላን ማረፊያዎች፤ባቡር ጣቢያዎች፤ ሕዝብ የሚያዘወትራቸዉ የገበያ ማዕከላትም ባይነ ቁራኛ እየተጠበቁ ነዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic