አዉሮጳን ያጥለቀለቀዉ የስደተኛ ጎርፍ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አዉሮጳን ያጥለቀለቀዉ የስደተኛ ጎርፍ

አዉሮጳን ያጥለቀለቀዉ የስደተኞች ጎርፍ የአዉሮጳ ኅብረትን አንድነት አናዉጦ የተመሠረተባቸዉን እሴቶችና መርሆዎችን ጥያቄ ዉስጥ እያስገባ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:34
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:34 ደቂቃ

የስደተኛ ጎርፍ በአውሮፓ

ከጦርነትና እልቂት አምልጠዉ ተገን ፍለጋ አዉሮጳ የሚገቡት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት ስደተኞች በርካታ በሚባሉ የአዉሮጳ መንግሥታት እንደስጋት ተቆጥረዉ በር ተዘግቶባቸዋል። ዛሬ አዉሮጳ በየቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች እምቢ ብለዉ የሚገቡባት ብቻ ሳትሆን የሕፃናት አስከሬን ከባህር ሲለቀም፤ ብዙዎችም በተሽከርካሪ ታጭቀዉ ሕይወታቸዉ ሲያልፍ፤ ሌሎች ደግሞ በባቡር ተገጭተዉ ሲሞቱና ሲቆስሉ የሚታዩባት የሰቆቃ ምድር ሆናለች። የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic