አዉሮጳን ያስጨነቀዉ የጸጥታ ጉዳይ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 24.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አዉሮጳን ያስጨነቀዉ የጸጥታ ጉዳይ

የአዉሮጳ ሃገራት ብራስልስ ዉስጥ ከደረሰዉ ጥቃት ወዲህ የክፍለ ዓለሙ ጸጥታ ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ከቷቸዋል። የቤልጂግ ፖሊስ ዛሬም ተፈላጊዉን ተጠርጣሪ እያሰሰ ነዉ። ከብራስልስ የወጡ ዘገባዎች አጥፍቶ ጠፊዎቹ ጥቃት አድራሾች የሀገሪቱን የኒኩሊየር መርሃግብር የመምታት እቅድ እንደነበራቸዉ ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:49
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:49 ደቂቃ

የጸጥታ ጉዳይ

ባለፈዉ ሳምንት በፓሪስ ጥቃት ተፈላጊዉን ግለሰብ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ዒላማቸዉን እንዲለዉጡ እንዳደረገቸዉም ያትታሉ። የቤልጅየም ባለስልጣናት በቂ የስለላ ክትትል ባለማድረግ እና በጀትም ባለመመደብ ትችት ገጥሟቸዋል። ቱርክ ከጥቃት አድራሾቹ አንዱን አስራ እንደነበር እና ወደ ቤልጅየም ሲመለስም ለባለስልጣናቱ ማሳወቋን ይፋ ማድረጓም ሌላ ስጋትና ትችትን ነዉ ያስከተለባቸዉ። እራሱን እስላማዊ መንግሥት ከሚለዉ ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸዉ በርካቶችም ኢራቅና ሶርያ እየደረሱ ወደአዉሮጳ መመለሳቸዉም ሌላዉ የስጋት ምክንያት ሆኗል። የአዉሮጳ ኅብረት የሀገር ዉስጥ ሚኒስትሮች ጸጥታን በተመለከተ ዛሬ ስብሰባ ያካሂዳሉ። ስለብራስልስ ዉሎና ስለስብሰባዉ ገበያዉ ንጉሤን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic