አዉሎ ነፋስ በመካከለኛዉ ምሥራቅ | ዓለም | DW | 09.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

አዉሎ ነፋስ በመካከለኛዉ ምሥራቅ

ሶሪያን፤ ሊባኖስን እስራኤልንና ቆጵሮስን ያዳረሰዉ አዉሎ ነፋስ በትንሹ ስምንት ሰዎችን ገድሏል። በመቶ የሚቆጠሩትን በሽታ ላይ ጥሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:12

አዉሎ ነፋስ ያደረሰው ጉዳት

በመካከለኛዉ ምሥራቅ አካባቢ ባለፉት ተከታታይ ወራት የተከሰተዉ ከፍተኛ ሙቀት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል። አለቅጥ የናረዉ የሙቀት መጠን ሰሞኑን ጋብ ማለቱ ከመሰማቱ አካባቢዉ በሌላ ተፈጥሯዊ መቅሰፍት ተመትቷል። አዉሎነፋስ። ሶሪያን፤ ሊባኖስን እስራኤልንና ቆጵሮስን ያዳረሰዉ አዉሎ ነፋስ በትንሹ ስምንት ሰዎችን ገድሏል። በመቶ የሚቆጠሩትን በሽታ ላይ ጥሏል።የእየሩሳሌሙ ወኪላችንን ዜናነሕ መኮንን እንደሚለዉ የዘንድሮዉን ዓይነት መቀትና አዉሎ ነፋስ በአካባቢዉ የሰባ አምስት ዓመት ታሪክ ታይቶ አይታወቅም።

ዜናነሕ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic