አወዛጋቢው የግብፅ ረቂቅ ሕገ መንግሥት | አፍሪቃ | DW | 03.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አወዛጋቢው የግብፅ ረቂቅ ሕገ መንግሥት

በግብፅ የሕገ መንግሥታዊው ጉባዔ ያረቀቀው አዲሱ የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ሕጋዊነት ጉዳይ አሁንም እንዳወዛገበ ይገኛል። የፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ደጋፊዎች፣ ፕሬዚደንቱ የሕገመንግሥታዊውን ፍርድ ቤት ሥልጣን ከሁለት

ሣምንታት በፊት የቀነሱበትን አዋጅ እና አዲሱን የሀገሪቱን ረቂቅ ሕገ መንግሥት ቢደግፉም፡ ብዙዎቹ የግብፅ ዜጎች ግን የፕሬዚደንቱን ርምጃና መሠረታዊ መብቶችን ይነፍጋል ያሉትን ረቂቅ ሕገ መንግሥት ተቃውመውታል።

ግብፅ በተከሠተው የሥልጣን ፉክክር፤ በሀገሪቱ በመላ የሚገኙ ዳኞች፤ አዲስ ህገ መንግሥት ለህዝበ -ውሳኔ በሚቀርብበት ድርጊት የማስተባበሩን ተግባር ላለማከናወን ሳያድሙ እንደማይቀሩ ተነገረ። የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር ፓርቲና የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሐመድ ሙርሲ፤የህግና ፍትኀ መ/ቤቶችን መብት በመጋፋታቸው የዳኞቹ ማኅበር ለታኅሳስ 6 የታቀደውን ህዝበ ውሳኔው ለማደራጀትና ለመቆጣጠር ፍላጎቱ እንዳልሆነ ነው የተመለከተው። ረቂቁ ህገ መንግሥት በአማዛኙ መሠረት የሚያደርገው ሸሪያን መሆኑ ታውቋል። ይህም ሲሆን በግብፅ  እስልምና የመንግሥት ሃይማኖት ተብሎ ይታወጃል ማለት ነው። የሙርሲን መርኅ በመቃወም ነገም በታህሪር አደባባይ ሰልፍ እንደሚደረግ ተገልጿል።  ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ ያነጋገርኩት የጄዳው ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ እንደሚለው፡ ይህም የሀገሪቱን ጊዚያዊ ሆኔታ አወሳስቦታል።

ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic