አወዛጋቢው የኢትዮጵያ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ | ኢትዮጵያ | DW | 11.08.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አወዛጋቢው የኢትዮጵያ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ

ረቂቅ አዋጁ ልዩ ልዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።ከመካከላቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰነዘሯቸው ጠንከር ያሉ ትችቶች ይገኙበታል።በተለይ በአዋጁ በምርጫ ስለሚወዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች የተቀመጠው ገደብና አገር አቀፍ እና የክልል የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት መሟላት አለበት የተባለው የመስራች አባላት ቁጥር በእጅጉ ካወዛገቡት መካከል ይጠቀሳሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 28:14

የኢትዮጵያ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ

ኢትዮጵያ ለ2012ቱ አጠቃላይ ምርጫ እየተዘጋጀች ይመስላል።ለዚህ እንደ አንድ ምልክት ሊወሰድ የሚችለው ለምርጫው ወሳኝ ተደርጎ የሚወሰደው የተሻሻለው የምርጫ ሕግ ረቂቅ፣ በቅርቡ ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት መቅረቡ ነው።በዚሁ ውይይት ላይም ረቂቅ አዋጁ ልዩ ልዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።ከመካከላቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰነዘሯቸው ጠንከር ያሉ ትችቶች ይገኙበታል።በተለይ በአዋጁ በእጩዎች ምዝገባ ሥር በምርጫ ስለሚወዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች የተቀመጠው ገደብ እና አገር አቀፍ እና የክልል የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት የተጠየቀው (የተቀመጠው) የመስራች አባላት ቁጥር በእጅጉ ካወዛገቡት መካከል ይጠቀሳሉ።በተለይ የ33 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ በሰጠው መግለጫ ረቂቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ሲል ወቅሷል። ተቃዋሚዎቹ  በተናጠልም እንዳሳወቁት ተቀባይነት የላቸውም ያሏቸውን እነዚህንና ሌሎች አንቀጾችን ያካተተው ረቂቅ ወደ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተመልሶ ውይይት እንዲደረግበትም ጠይቀዋል።ረቂቁን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ በገለልተኝነት እንደሚሰራ እና የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን እንደማያገለግል አስታውቆ ጥቅል ነው ያለው የፓርቲዎቹ ጥያቄ ዘርዘር ብሎ እንዲቀርብ አሳስቧል።የዛሬው እንወያይ ከአሁኑ ማወዛገብ በጀመረው «በኢትዮጵያ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ» ምንነት እና በረቂቁ ላይ በቀረቡበት ትችቶች ላይ ያተኩራል።በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወያዩልን ሦስት እንግዶች ጋብዘናል።እነርሱም ዶክተር ጌታሁን ካሳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣የቦርድ አባል፤አቶ ሙላቱ ገመቹ አራት ፓርቲዎችን ያሰባሰበው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፣መድረክ በአጭሩ ስራ አስፈጻሚ  እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም አቶ ተማም አባቡልጎ ጠበቃ እና የሕግ ባለሞያ ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ፥

ኂሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic