አወዛጋቢው የአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ  | አፍሪቃ | DW | 27.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

አወዛጋቢው የአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ 

በአሜሪካን መንግሥት የሚደገፈው ይህ የገንዘብ ዋስትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ግምት ውስጥ ባለማስገባት በዘርፉ ባለሞያዎች እና በመገናኛ ብዙሀን ተተችቷል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:02

አወዛጋቢው የአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ 

.
አንድ ዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ድርጅት ሰዎችን እንደ ባሪያ በማሠራት በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በአካባቢ ብከላ ለሚወነጀሉ የአፍሪቃ የማዕድን ማውጫ ኩባንያዎች ቁሳቁሶችን ለሚያቀርብ ኩባንያ የ315 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መስጠቱ እያወዛገበ ነው ። ጋርድያን የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ኮኔል የተባለው ኩባንያ ከሰሀራ በስተደቡብ ከሚገኙ የሰባት ሀገራት የማዕድን ኩባንያዎች ጋር ውሎችን ማካሄድ እንዲችል የአሜሪካን የወጪ እና ገቢ ንግድ ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ ከጎርጎሮሳዊው 2007 እስከ 2015 የመድን ዋስትና ድጋፍ አድርጎለታል ። መሰል ድጋፍ ካገኙት የኩባንያው ሥራዎች አንዱ ለኤርትራ ማዕድን ማውጫ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ያገኘው የዋስትና ድጋፍ ነው ። በአሜሪካን መንግሥት የሚደገፈው ይህ የገንዘብ ዋስትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ግምት ውስጥ ባለማስገባት በዘርፉ ባለሞያዎች እና በመገናኛ ብዙሀን ተተችቷል ።መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አለው ። 
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic