አወዛጋቢው የመተዳደሪያ ደንብ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 13.12.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አወዛጋቢው የመተዳደሪያ ደንብ

እ.ኤ.አ. በሁለት ሺህ አምስት በፈረንሳይና በኔዘርላንድ ሕዝበ ድምፅ ውድቅ የተደረገው የአውሮጳ ህብረት የመተዳደሪያ ደንብ ዛሬ በሊዝበን ፖርቹጋል ተፈረመ።ለመሆኑ ይህ የተሻሻለው የመተዳደሪያ ደንብ ከቀድሞው ህግ የሚለየው በምንድን ነው?

የሊዝበኑ ጉባኤ በከፊል

የሊዝበኑ ጉባኤ በከፊል


ሃያ ሰባቱ የአውሮጳ አባል አገራት ከአንድ ዓመት በኃላ የሚተዳደሩበትን አዲስ ህግ ለማፅደቅ ሐሙስ ታህሳስ ሶስት በፖርቹጋል ሊዝበን ተሠይመዋል።ሆኖም ሁለቱን አዲስ ህግጋት ሃያ ሰባቱ አባል አገራት ተቀብለውት ለማፅደቅ ብዙ ጥረትን መጠየቁ አልቀረም።አንደኛው ህግ መሠረታዊ የሆነው ሲሆን፤ሁለተኛው ደግሞ ኀብረቱ የሚተዳደርበት ዝርዝር ህግ ነው።ህግጋቱ ከምንም በላይ የህብረቱ አባል ላልሆኑት ሌሎች የአውሮጳ አገራት እንደሚጠቅም ተገልጿል።በርግጥም ከዚህ አዲስ ህግ ውጪ የባልካን አገራትም ሆኑ ቱርክ ህብረቱን ሊቀላቀሉ አይችሉም።

የዚህlወሳኝ ህግ ረቂቅ ግን በፈረንሣይና ኔዘርላንድ ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከሁለት ዓመታት በላይ ተቀብሮ ቆይቶዋል።ሆኖም ሐሙስ ታህሳስ ሶስት ለውሳኔ በድጋሚ ሲቀርብ ከቀድሞው ረቂቅ ብዙም የተቀየረ ሆኖ አልነበረም።በእርግጥ አባል አገራቱን የሚያስታውሱ ነገሮች ከረቂቁ ውስጥ ተነስተዋል።ማለት ሠንደቅ ዓላማ፣ብሔራዊ መዝሙር፣የውጭ፣ጉዳይ ሚንስትሩ ማዕረግ እና የተወሰኑ ነገሮች።የድምፅ አሰጣጥ ስርአቱና ህገ መንግስቱ ግን በፊት ውድቅ ከተደረገው ረቂቅ ህግ ጋር በምንም የሚለዩ አይደሉም።

እንግሊዝና ፖላንድ መሰረታዊ ህጉን የሚመለከተው ክፍል የአዲሱ ረቅቂ ህግ አባል እንዲሆን አይፈልጉም።በተጨማሪም እንግሊዝ የአገር ውስጥ ጉዳይና የፍትህ ስርዓቱን በተመለከተ ራሷን ነፃ አድርጋለች።አዲሱ ረቂቅ ህግ ለተግባራዊነቱ በሃያ ሰባቱም አባል አገራት ፀድቆ መፈረም ይኖርበታል።ፈረንሣይ አሁንም ጉዳዩን በህዝበ ድምፅ ለመወሰን ፈልጋለች።ኔዘርላንድና ዴንማርክ ውሳኔያቸው አልታወቀም።በአየርላንድ ብቻ የህዝበ ድምፅ ውሳኔው ተጠቃሏል።

ሆኖም ሀሙስ ታህሳስ ሶስት በሊዝበን ፖርቹጋል የተሰየመው የአውሮጳ ህብረት፤ከሁለት ዓመት በላይ ሲያወዛግብ የከረመውን አዲሱን የአውሮጳ ህብረት መተዳደሪያ ረቂቅ ህግ በስተመጨረሻ ተቀብሎ አፅድቆታል።ይህ በመሆኑም እ.ኤ.አ. ሠኔ ሁለት ሺህ ዘጠኝ በሚሰየመው ቀጣዩ የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ላይ ተግባራዊ ይሆናል።