አካባቢያዊ ጸረ የዩጋንዳ ዓማጽያን ቡድን ዘመቻ | ኢትዮጵያ | DW | 06.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አካባቢያዊ ጸረ የዩጋንዳ ዓማጽያን ቡድን ዘመቻ

በዩጋንዳ መንግስት አንጻር ከሀያ ዓመት በላይ የተዋጋው ኤል አር ኤ አሁን አካባቢውን በጠቅላላ ያሳሰበ ቡድን ሆኖዋል።

default

በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል፡ በስብዕና አንጻር በተፈጸመ ወንጀል በእስራት በሚፈለጉት ጆሴፍ ኮኒ የሚመራው ኤል አር ኤ ከጎረቤት ሀገሮች በመንቀሳቀስ፡ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፑብሊክ፡ በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፑብሊክ እና በደቡብ ሱዳን ትልቅ ጥፋት በማድረስ ላይ ይገኛል። በተመድ ዘገባ መሰረት፡ ቡድኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ሲገድል፡ ከአራት መቶ ሺህ የሚበልጡ አፈናቅሎዋል። በዚህም የተነሳ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አራት ሀገሮች አሁን ለችግሩ ባንድነት መፍትሄ ለማፈላለግ ወስነዋል።


አርያም ተክሌ