አከራካሪዉ የጀርመን ግብር አጭበርባሪዎች ጉዳይ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 05.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አከራካሪዉ የጀርመን ግብር አጭበርባሪዎች ጉዳይ

በጀርመን የቀረጥ አጭበርባሪዎች ስም ዝርዝርን ለማግኘት የሚደረገዉ ሙከራ በጀርመን ባለስልጣናት ዘንድ ሰሞኑን ትልቅ የመነጋገርያ ርእስ ሆኖ ሰንብቶአል።

default

1500 ያህል ግለሰቦችን የስም ዝርዝር እና ሌላ የመረጃ ዶሴዎችን የያዘ ሴዴ የጀርመን መንግት መግዛቱ ወንጀል ነዉ አይደለም ትልቅ የክርክር ርዕስ ሲሆን ሌላዉ ግለሰቦቹ አልያም ድርጅቶች ገንዘባቸዉን ከአገሪቷ አዉጥተዉ በስዊዘርላንድ ባንክ ደብቀዉ በማስቀመጥ የአገሪቷን ኢኮኖሚ በማቃወስ ማጭበርበራቸዉ፣ መንግስትን ብቻ ሳይሆን ከትንሽ እስከ ትልቅ የሆነዉን ነዋሪንም ነዉ ያስቆጣዉ። ይህ በስርቆት የተገኘ የመረጃ ዶሲ መንግስት መግዛት ይኖርበታል አይኖርበትም በክርክር ላይ ነዉ። መንግስት መረጃዉን ሰርቀዉ ካገኙት ግለሰቦች ዶሴዉን ከገዛ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሎዮን ይሮ እንደሚያወጣ ሲገለጽ፣ መረጃዉ መንግስት እጅ ከገባ በኋላ እና ግለሰቦቹ ከተጋለጡ መንግስት ከመቶ ሚሊዮን ይሮ በላይ የተጭበረበረ ገንዘብ ኪሱ እንደሚያስገባ ከወዲሁ እየተነገረ ነዉ። አርያም ተክሌ ዝርዝር ዘገባ ይዛለች አርያም ተክሌ፣ አዜብ ታደሰ ፣ ሂሩት መለሰ Aryam Abraha ,Azeb Hahn