አንፃራዊው የህፃናት ድህነት በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አንፃራዊው የህፃናት ድህነት በጀርመን

በኢንዱስትሪ ከበለፀጉ አገራት ተርታ የምትሰለፈው ጀርመን ህፃናትን ለማሳደግ አመቺ በተባሉ ሃገራት ማነፃፀሪያው ሰንጠረዥ አስራ አንደኛ ደረጃ ነው ያገኘችው ።

default

ምንም እንኳን ጀርመን ህፃናትን ተንከባክቦ በማሳደግ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣት ሀገር ብትሆንም በሃገሪቱ የኑሮ ደረጃ መመዘኛ መሰረት የድህነት ህይወት ውስጥ የሚገኙ ህፃናት ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም ። በጀርመን ፌደራል ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት ዘገባ መሠረት ከጀርመን ህፃናት 15 በመቶ ያህሉ ማለትም ከ 6 ልጆች አንዱ በጀርመን ህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ በአንፃራዊነት የተጎሳቆለ ኑሮ ውስጥ ይገኛል ። ለዚህ ዓይነቱ ህይወት በይበልጥ ከሚጋለጡት ህፃናት ውስጥ በተለይ በአንድ ወላጅ ማለትም በእናት ወይም በአባት ብቻ የሚያድጉ ህፃናት ይገኙበታል ። ከነዚህ ውስጥ ወደ 37 በመቶ የሚሆኑት በሀገሪቱ ለድህነት ከተቀመጠው ደረጃ በታች በሆነ ኑሮ ውስጥ እንደሚገኙ ይኽው መረጃ ያመለክታል ። በጀርመን የህፃናት ድህነት ሲባል ግር ማሰኘቱ አይቀርም ። በተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር ዩኒሴፍ የጀርመን ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ሩዲ ታርኔደን ለዶቼቬለ የአማርኛው ክፍል በሰጡት ማብራሪያ በጀርመን የህፃናት ድህነት ሲባል በሶስተኛው ዓለም ከሚታወቀው ድህነት የተለየ መሆኑን አስረድተዋል ።

ሒሩት መለሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic