አንጎላ እና አዲሱ አከራካሪ ህገ መንግስት | ኢትዮጵያ | DW | 23.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አንጎላ እና አዲሱ አከራካሪ ህገ መንግስት

የእግር ኳስ ቡድኖች በጠቅላላ ጨዋታው የሚራዘምበትን ሁኔታ ለማስቀረት ነው ለወትሮው የሚፈልገው። በፖለቲካው ዘርፍ ሲታይ ግን በስልጣን ላይ ያሉ ብዙ ፖለቲከኞች ይህንኑ ስልጣናቸውን ለማራዘም ነው የሚጥሩት።

default

የአንጎላ ፕሬዚደንት ኾዜ ዶስ ሳንቶሽ

አንጎላን ካለፉት ሰላሳ ዓመታት ወዲህ የሚመሩት ፕሬዚደንት ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶሽ በዚሁ አሰራር የተካኑ ፖለቲከኛ ናቸው። እአአ በ 1992 ዓም ብቻ ነበር ራሳቸውን ለምርጫ በተወዳዳሪነት ያቀረቡት። ግን ያኔ፡ እንደሚታወሰው፡ የእርስበርሱ ጦርነት እንደገና በመፋፋሙ የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ብቻ ነበር የተካሄደው። እአአ ከ 2002 ዓም ወዲህ አንጎላ ውስት ሰላም ሰፍኖዋል፤ እና አንጎላ ዜጎች ከዚያን ጊዜ ጀምረው ቃል የተገባላቸው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚደረግበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ፕሬዚደንቱ ግን ምርጫ ለማካሄድ ፍጹም ሀሳብ የሌላቸው ከመሆኑም ሌላ፡ የህዝቡ ትኩረት በበሀገሩ በሚካሄደው የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ላያ ያረፈበትን ሁኔታ ከለላ በማድረግ ስልጣናቸውን ማራዘም የሚችሉበትን አንቀጽ በህገ መንግስቱ ለማስፈር ሙከራ ይዘዋል።

አርያም አብርሃ/ዩሀንስ ቤክ