1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንድ ዓመት የደፈነው ጦርነት በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ጥቅምት 28 2014

ሰሜን ኢትዮጵያ፤ ትግራይ ክልል የጀመረው ጦርነት በያዝነው ሳምንት አንድ ዓመቱን ደፍኗል። ጦርነቱ ወደ አፋርና አማራ ክልሎች አድማሱን አስፍቶ ቀጥሏል። እስካሁን በግጭቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ሕይወት አልፏል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤት ቀዬያቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል፤ የዕለት ርዳታ ጠባቂዎች ለመሆንም ተገደዋል።

https://p.dw.com/p/42eNz
Äthiopien Tigray-Krise | Armee
ምስል Ben Curtis/AP/picture alliance

አድማሱን አስፍቶ አሁንም ቀጥሏል

ሰሜን ኢትዮጵያ፤ ትግራይ ክልል የጀመረው ጦርነት በያዝነው ሳምንት አንድ ዓመቱን ደፍኗል። ጦርነቱ አድማሱን አስፍቶ አሁንም ቀጥሏል። እስካሁን በግጭቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ሕይወት አልፏል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤት ቀዬያቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል፤ የዕለት ርዳታ ጠባቂዎች ለመሆንም ተገደዋል። ከሰኔ 21 ቀን፣ 2013 ዓ.ም በፊት በግጭቱ የደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ለአራት ወራት በጣምራ ያካኼዱትን ምርመራ ውጤትም ከሰሞኑ ይፋ አድርገዋል። በዚህም በግጭቱ በተሳተፉ ሁሉም ኃይላት ከፍተኛ የተባለ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸሙንም ተቋማቱ ዐሳውቀዋል። ጦርነቱ ከ1 ዓመት በኋላ፦ ከተቀሰቀሰበት ከትግራይ ክልል ወጥቶ በርካታ አካባቢዎችን በተለይም የአማራ እና አፋር ክልሎችን አዳርሷል፤ ተስፋፍቷልም። ከቀናት በፊትም በሚንሥትሮች ምክር ቤት የተደነገገውን ለስድስት ወራት የሚዘልቀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጽድቆታል። ጦርነቱ ቆሞ ወደ ድርድር እንዲገባ በተደጋጋሚ ጥሪ የሚያቀርቡ ወገኖች ቢኖሩም ተፋላሚ ወገኖች በውጊያው ገፍተውበታል። ሕወሓት ጦርነቱን ሕዝባዊ ማድረጉን እና የታጣቂዎቹ ግስጋሴን ተከትሎ መንግሥትም ሕዝቡን «ክተት» ብሎ መጠነ-ሰፊ እንቅስቃሴው ቀጥሏል። ይህ የጦርነቱ መቋጫ እንዴት ይሆን የሚለውን ጥያቄ አጭሮ እያነጋገረ ነው። «አንድ ዓመት የደፈነው ጦርነት በኢትዮጵያ»፦ የእንወያይ መሰናዶዋችን የሚያጠነጥንበት ርእሰ ጉዳይ ነው።  በውይይቱ 3 እንግዶች ተሳታፊ ናቸው። 

ሙሉ ውይይቱን በድምፅ ማጫወቻው መከታተል ይቻላል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ