አንድነት የገጠመው ሳንክና የሰልፉ ዝግጅት | ኢትዮጵያ | DW | 26.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አንድነት የገጠመው ሳንክና የሰልፉ ዝግጅት

የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ ኣበባ ከተማ ለማካሄድ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማጨናገፍ መንግሥት ከወዲሁ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሰልፉን ግን ከማካሄድ ወደኃላ እንደማይል የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ርነጋሶ ጊዳዳ አስታወቁ ።

ዶ/ር ነጋሶ

ትላንት ለተወሰነ ጊዜ በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውንም አረጋግጠው ነገር ግን ያደረሱብን እንግልት የለም ብለዋል የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳ ዳ ዛሬ

ለዶቸቬሌ እንደገለጹት ፓርቲያቸው ኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ለፊታችን እሁድ

በአዲስ ኣበባ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል በዚሁመሰረት

የተቀናጀ የቅስቀሳ ስራም ተጀምረዋል ቅስቀሳውደግሞ የኣንድነት ለዲሞክራሲ

እና ፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበሩ ዶ/ርነጋሶ ጊዳዳ እንደገለጹት ሶስት ኣይነት

መልክ ያለው ነው አንደኛው የፓርቲው አባላት አስራ አምስት እራሳቸውን እየሆኑ በተከራዩ

ሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ኣማካንነት በየክፍለ ከተማው እየተዘዋወሩ በራሪ ወረቀቶችን

እንዲበትኑ ሁለተኛው በእነዚህ ተሽከርካሪዎች ላይ የጥሪ ፓስተሮች እንዲለጠፉ ማድረግ

እና ሶስተናው በደግሞ ድምጽ ማጉያዎች ኣማካይነት ከተሽከርካሪዎቹ ላይ

ጥሪውን ማስተጋባት ናቸው በዚሁ መሰረት ቅስቀሳው ተጀምሮ ሳለ ዶ/ር ነጋሶ እንደሚሉት

ከትላንት በስትያ ማክሰኖ ነበር ችግሮች ማጋጠም የጀመሩት

Dr. Negasso Gidada

የኣንድነት ፓርቲ ኣመራር በችግሩ ላይ ከመከረ በኋላ ዶ/ር ነጋሶ እንደገለጹት አባላቱ

በሚታሰሩበት ስፍራ ዓመራሩም እየተከተለ ከተቻለ ለማስፈታት ካልሆነም እነሱን ኣስወጥቶ

ለመታሰር እና ይህም ካልተቻለ አብሮ ለመታሰር ውሳኔ ኣስተላልፈዋል በትላንትናው እለትም

እንደዚሁ ወደ ኮልፌ ሽሮሜዳ እና ንፋስስልክ ኣቅጣጫዎች ሶስትየቅስቀሳ ቡድን እንደተሰማራ

ወዲያውኑ እስራት ተጀመረ ዓመራሩም በውሳኔው መሰረት ተከትሎ ይሄዳል ዶ/ር ነጋሶም በዚሁ

መሰረት ነበር ወደ ሽሮሜዳ ያቀኑት

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚሉት ደግሞ የአዲስ ኣበባ ኣስተዳደር በነጋሪትጋዜጣ

ባይታወጅም ውስጥ ውስጡን እንደ መመሪያ የሚተላለፍ ደምብ ኣውጥተዋል

እንደ ሰልፉ ሁሉ ለማንናውም የቅስቀሳ ስራም ፈቃድ ያስፈልጋል የሚል

ታግተው በቆዩባቸው ሳዓታት የደረሰባቸው አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ በደልካለ

ዶ/ርነጋሶንጠይቄኣቸውነበር

በጉዳዩ ላይ የበኩላቸውን ምላሽ እንዲሰጡ በአዲስኣበባ ፖሊስ ኮሚሺን ወደጉለሌክ/ከተማ

የፖሊስ መምሪያደውዬነበር ነገርግንስልኩንያነሱትግለሰብ ሌላው ቀርቶ ስማቸውንም ሆነ

ማዕረጋቸውን ለመግለጽ ካለመፈለጋቸውም በላይ ዶ/ርነጋሶ በጭራሽ ወደጣቢያውኣልመጡም

የምናውቀው ነገር የለም በማለት ነበር ስልኩን የዘጉት

ጃፈር አሊ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic