አነጋጋሪው የደቡብ ሱዳን የሰላም ውል | አፍሪቃ | DW | 22.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አነጋጋሪው የደቡብ ሱዳን የሰላም ውል

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ታቅዶ የነበረው የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ የአንድነት መንግስት አለመምሠረት በሃገሪቱ ሰላም ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት እንዳያደናቅፍ እያሰጋ ነው ። የደቡብ ሱዳን አማፅያን መሪ ሪክ ማቸር በሳምንቱ መጀመሪያ ጁባ ይገባሉ ተብለው ሲጠበቁ መቅረታቸው ብዙ የተለፋበትን የሰላሙን ተስፋ አደብዝዞታል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:58
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:58 ደቂቃ

አነጋጋሪው የደቡብ ሱዳን የሰላም ውል

ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ሁለቱም ወገኖች የሽሽግሩን መንግሥት ምሥረታ እንዲያፋጥኑ ጥሪ አቅርቧል ። የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት የሚቆጣጠርና የሚገመግመው ዓለም አቀፍ ኮሚሽን ሁለቱ ወገኖች እስከ ነገ እንዲስማሙና ማቻርም ጁባ እንዲሄዱ ቀነ ገደብ አስቀምጧል ።
ሰኞ ሚያዚያ 10 ፣ 2008 ዓም ነበር የደቡብ ሱዳንን የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ቀጠሮ የተያዘው ። የአማፅያኑ መሪ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በቃለ መሃላው ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ባለፈዉ ሳምንት አርብ ነበር ደቡብ ሱዳን ገቡ የተባለው ። ይሁንና በዚህ ሳምንት ሰኞ የጁባ ጉዞአቸው ለማክሰኞ መተላለፉ ተነገረ ። እንደተባለው ግን ማቸር ማክሰኞም ጁባ አልሄዱም ፤እንዲያውም የጁባ ጉዞአቸውን ላልተወሰነ ጊዜ መሰረዛቸው ተሰማ ። አማፅያኑ እንዳሉት ማቻር ጁባ ያልሄዱት ዓለም ዓቀፍ የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው ከፍተኛ ጀነራላቸው ሲሞን ጋትዌች ከኢትዮጵያ ወደ ጁባ መብረር በመከልከላቸው ነው ። የደቡብ ሱዳን መንግሥት ደግሞ ጋትዌች ከሰላም ስምምነቱ ውጭ ከባድ የጦር መሣሪያዎችና ተጨማሪ 260 ወታደሮቻቸውን ይዘው ርዕሠ-ከተማ ጁባ ለመግባት በመፈለጋቸው ምክንያት የማቻርን ጉዞ መከልከሉን አስታውቋል ። \

በውዝግቡ ሰበብ የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግሥት ምሥረታ መዘግየት በሃገሪቱ ሰላም ለማውረድ በሚደረገው ጥረት ላይ ጥላአጥልቷል ። አቶ አበበ አይንቴ፣በኢትዮጵያ የሰላም እና ልማት ዓለም አቀፍ ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ እንደሚሉት የመንግሥት ምሥረታው መዘግየት የሰላሙን ጥረት አውኳል ፤ የህዝቡንም ስቃይ እያራዘመው ነው ።
በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት መሠረት የሚመሰረተው መንግሥት እድሜ 30 ወራት ነው ። ከዚያ በኋላም ምርጫ ለመጥራት ነው የታሰበው ። ማቻር ጁባ አለመሄዳቸው ለሰላም ስምምነቱ አደጋ ነው ሲል የስምምነቱን ተግባራዊነት የሚቆጣጠረው ኮሚሽን አሳስቧል ። በተቻለ ፍጥነት ወደ ጁባ ካልተመለሱም የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነትን ማጓተቱ እንደማይቀር ነው የተገለፀው ።ዩናይትድ ስቴትስ ማቻር ጁባ ባለመሄዳቸው ቅሬታዋን ገልፃለች ። የተመድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በበኩሉ ሁለቱም ወገኖች በአፋጣኝ የሽግግሩን መንግሥት እንዲመሰርቱና የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል ። ኪርና ማቻር የፈረሙትን የሰላም ስምምነት በተግባር እንዲተረጉሙ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ይላሉ አቶ አበበ ።
የደቡብ ሱዳን የሰላሙ ጥረት ለመጓተቱ ፣ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚያውኩ ወገኖች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ አለመወሰዱን አንደ ምክንያት የሚያነሱ ወገኖች አሉ ። አቶ አበበ እንደሚሉት ግን ከነዚህ እርምጃዎች ይልቅ ውጤት ሊያመጣ የሚችለው ሳልቫ ኪርና ማቻር ለህዝባቸው ሲቆሙ ብቻ ነው ።

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic