አነጋጋሪው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ | ኢትዮጵያ | DW | 03.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አነጋጋሪው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው ኦሮምያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ያስከብራል የተባለዉ ረቂቅ አዋጅ እያነጋገረ ነው። መንግስትና የአዋጁ ደጋፊዎች፣ አዋጅ «መንግስት ህዝባዊ ለመሆኑ መገለጫ መሆኑን»ደጋግመው ቢጠቅሱም ተችዎች ግን ይህ አዋጅ በይዘቱም ሆነ በዓላማዉ የኦሮምያን ልዩ ጥቅም በሚያስከብር ሁኔታ አልተረቀቀም ሲሉ ይከራከራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:52

የኦሮምያ ልዩ ጥቅም

የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክርቤት ባለፈዉ ማክሰኞ ኦሮምያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ያስከብራል ያለውን አዋጅ አርቅቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት መርቶታል።

ይህ ረቂቅ አዋጅ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም ሆነ በሌሎች የዉይይት መድረኮች ከፍተኛ የመወያያ ርዕስ ሆኗል። የአዋጁ ደጋፊዎች እና ተችዎች በረቂቁ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየሰነዘሩ ነው።የመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ምኒስትር ዶክተር ነገር ሌንጮ ረቅቅ አዋጁ «በታሪክ አጋጣሚ የተከሰቱ የታሪክ መዛባትን እያነሳን ወደኋላ የምናስብበት ሳይሆን ወደ ፊት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት እንድናደርግ የሚያግዝ» እንደሆነና «ልዩ ምክንያት ኖሮ ሳይሆን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመሆኑ ነው» ብሎ መናገራቸዉ ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሼን ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረገ ይህ አዋጅ ትልቅ ዉጤት ነው ሲሉ የፌስቡክ ደረገጻቸዉ ላይ አስፍረዉ ፣ ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ዉይይት ከተደረገ በኋላ እንደሚፀድቅም አስታውቀዋል።

ተችዎች ግን ይህ አዋጅ በይዘቱም ሆነ በዓላማዉ የኦሮምያን ልዩ ጥቅም በሚያስከብር ሁኔታ አልተረቀቀም ሲሉ ይከራከራሉ። በአሜሪካ መቀመጫውን ያደረገዉ የኦሮሚያ ጥናት ማህበር ባለፈዉ ዓርብ ባወጣዉ መግለጫ ረቅቅ አዋጁ የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎት እንደማያሟላና ልዩ ጥቅሙም በህገመንግስቱ ዉስጥ በተደነገገዉ መሰረት አልተቶረገመም ሲል ረቂቅ ህጉን ተችተዋል። የህግ ባለሙያ አቶ ተማም አባቡልጉም ስለ አዋጁ ለዶይቼ ቬሌ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ረቅቅ አዋጁን አስመልክቶ የዋትስአፕና የፌስቡክ ተከታታዮቻችንን ሃሳብ ተቀብለን ነበር። በዋትስአፕ ላይ ስሙን ሳይጠቅስ የድምፅ አስተያየት የላከልን ግለሰብ አዋጁ ዉይይት ያስፈልገዋል ይላል። ሌላ አስተያየት ሰጭ መንግስት ህዝብን ለማከፋፈልና የኦሮሞን ወጣቶች የትግል ስሜት ለማቀዝቀዝ የታቀደ ነዉ ይላሉ።

አቶ ኤባ ጋዳ የሚል የፌስቡክ ስም የያዙ አዋጅ መንግስት ሕበረተሰቡ ያነሳዉ ሕጋዊ ጥያቄ ማስተናገድ አለመቻሉ ማሳያ ነዉ ይላሉ። በዋትስአፕም ላይ ስማቸውን ያልጠቀሱ አስተያየት  ሰጭ «ይህ አዋጅ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመመለስ ፊፁም በቂ አይደለም» የሚል መልዕክት ልከውልናል።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic