አነጋጋሪው የኢትዮጽያ የምጣኔ ሃብት ይዞታ፣ | ኢትዮጵያ | DW | 08.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አነጋጋሪው የኢትዮጽያ የምጣኔ ሃብት ይዞታ፣

የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም በእንግሊዘኛዉ ምህጻሩ IMF በመባል የሚታወቀዉ ድርጅት በያዝነዉ ወር ባወጣዉ መግለጫ የኢትዮያ የምጣኔ ሃብት እድገት በ 7.2 እጅ ከመቶ ያደገ መሆኑን ቢገልጽም እድገቱ አጥጋቢ አለመሆኑን በማያያዝ አትቶአል።

default

6,2 ሚልዮን ያህል ሰዎች በተራቡባትና ድርቅ በተጠናወታት ኢትዮጵያ፣ 10% የኤኮኖሚ ዕድገት ይገኛል መባሉ ያስነሣው ክርክር፣

በሌላ በኩል በያዝነዉ ሳምንት የኢትዮጽያ ፊደሪሽን ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተከፈተበት ወቅት የኢትዮጽያዉ ፕሪዝዳንት ግርማ ወልደ ጌዮርግስ የኢትዮጽያን ኢኮነሚ በ 10 እጅ ማደጉን ገልጸዋል። ይህም የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት IMF ካለዉ እድገት በ 2 እጅ ከፍ ያለ ነዉ። የኢትዮጽያ የኢኮነሚ እድገት አለ! እየታየም ነዉ! የሚባለዉን ገለጻም ሆነ፣ የኢትዮጽያን መንግስት መግለጫ፣ በርካታ የኢኮነሚ ምሁራንን እና ሞያተኞችን እያነጋገረ ነዉ። ዝርዝሩን የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ያቅርብልናል።

ድልነሳ ጌታነህ/አዜብ ታደሰ/

ተክሌ የኋላ