አነጋጋሪው የአፍሪቃ ነፃ ፓስፖርት  | አፍሪቃ | DW | 27.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

አነጋጋሪው የአፍሪቃ ነፃ ፓስፖርት 

አፍሪቃውያንን በአባል ሀገራት ውስጥ በነፃ መዘዋወር ያስችላል ስለተባለው ነጻ ፓስፖርት ጉዳዩ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኤኮኖሚ እና የፖለቲካ ጉዳዮች አጥኚ እና ተንታኝ ፕሮፌሰር ደሳለኝ ራህማቶ ከነጻ ዝውውሩ በፊት በአባል አገራት መካከል የንግድ ትስስሩን እና ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን ማጠናከሩ መቅደም ይኖርበታል ብለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:59

የአፍሪቃ ፓስፖርት

የአፍሪቃ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት በክፍለ ዓለሙ የሰዎች እና የሸቀጦች ነጻ ዝውውር ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊዎቹ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠየቀ ። ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጉዳይ ላይ የተነጋገረው ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ነፃ የሰዎች እና የሸቀጦች ዝውውር የአፍሪቃን ውህደት ያመቻቻል ያፋጥናልም ሲል አስታውቋል ። አፍሪቃውያንን በአባል ሀገራት ውስጥ በነፃ መዘዋወር ያስችላል ስለተባለው ነጻ ፓስፖርት ጉዳዩ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኤኮኖሚ እና የፖለቲካ ጉዳዮች አጥኚ እና ተንታኝ ከነጻ ዝውውሩ በፊት በአባል አገራት መካከል የንግድ ትስስሩን እና ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን ማጠናከሩ መቅደም ይኖርበታል ብለዋል ። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ   

Audios and videos on the topic