አነጋጋሪው የቤርሙዳ ባህር | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 04.04.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

አነጋጋሪው የቤርሙዳ ባህር

Vincent H. Gaddis የተባሉ ጸሐፊ፣ እ ጎ አ በ 1964 ዓ ም፣ Argosy ለተሰኘ መጽሔት በቤርሙዳ ባህር፣ መርከቦችና አኤሮፕላኖች፣ መንስዔው ሊታወቅ ባልቻለ አደጋ ደብዛቸው ጠፍቶ ቀርቷል ሲሉ አንድ መጣጥፍ ካቀረቡና ቀጥለውም ፤

default

Invisible Horizons  (የማይታዩ አድማሶች)  እና  True Mysteries of the Sea(እወነተኛው የባህሩ ምሥጢሮች)በሚሉ አርእስት መጻሕፍት ከጻፉ በኋላ፣ ከማያሚ ፍሎሪዳ በስተደቡብ ምሥራቅ እስከ ሳን ሁዋን ፖይርቶ ሪኮ፤ ከ ሳን ሁዋን በቀጥታ በስተሰሜን እንዲሁም ከማያሚ በስተሰሜን ምሥራቅ ቤርሙዳ  ድረስ ፣ በእነዚህ 3 ማዕዝናት ውስጥ የሚገኘው የአትላንቲክ ክፍል የሆነው ባህር ፣ በ 20ኛው ክፍለ ዘመን  ከሳይንሳዊ ትንተና በወጣ መልኩ የተለየ ምትኃታዊ ኃይል ያለው ነው እየተባለ ሲነገርለት ኖሯል።
የዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ፤ ስለ ቤርሙዳ ባህርና ስለሚነገርለት አደገኛነት  ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ለጠየቁ አንድ አድማጭ መልስ ይሆናል ያለውን ከዚህ ቀደም  እ ጎ አ መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓ ም የተሠራጨውን ያቀርባል። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ---
ተክሌ የኋላ--

12mph. (AP Photo/HO)


 በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ  መካከል ፤ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወዲህና ወዲያ ማዶ የአየርና  የባህር  ትራፊክ እጅግ የበዛበት መሆኑ ሲታሰብ፣ እስካሁን የደረሰው አደጋ  የተለየ ግምት የሚሰጠው አይደለም። በካሪቢያን ባህርና ባካባቢው እንደሚታየው ሁሉ በሌሎች አንዳንድ የዓለም ክፍሎችም፣ ብርቱ ማዕበል የሚከሠትባቸው፤ ጉም፤ ጭጋግ  የሚበዛባቸው አሉ። ከባህር ወለል የሚነሳ የምድር ነውጥ፤ እሳተ ገሞራ፤ የተፈጥሮ ጋዝና  የመሳሰለውም ሊያስከትል የሚችለውን እንከን ልብ ይሏል። በተጠቀሰው ቤርሙዳ ባህር አካባቢ፤ Gulf Stream የተሰኘው፤ ከሜክሲኮ ባህረ ሰላጤ እስከ ሰሜናዊው የምድር  ዋልታ  እንደ ትልቅ ወንዝ ፣ ሞቃትና ቀዝቃዛ የውቅያኖስ ውሃ እያዘዋወረ እንደሚጎርፍም የታወቀ ነው። ይህ ደግሞ ለመርከብ ጉዞ አመቺ የሚባል አይደለም።
በ 20ኛው ክፍለ ዘመን በቤርሙዳ ባህር ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች አኀዝ ከ 1,000 እምብዛም የላቀ አይደለም። በአማካዩ፣ በዓመት 10 ያህል ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ማለት ነው።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 04.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14Xul
 • ቀን 04.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14Xul