አነጋጋሪው የማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና | ዓለም | DW | 24.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

አነጋጋሪው የማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና

ከ 4 ዓመት ገደማ በፊት፤ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙ አንድ የኔልሰን ማንዴላ ድርጅት ዋና ተመራማሪ፤ ማንዴላን በማሠልጠን ያገዙ በሕይወት የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ ጠይቀው ያሰባሰቡት መረጃ ፣ ማንዴላ ከእሥራኤላውያን ጋር ግንኑነት እንደነበራቸው የሚያረጋግጥ አንዳችም እውነታ አልተገኘበትም።

ማንዴላን የጨበጣ ውጊያ ፣ የጦር መሣሪያ፣ አፈታትና አገጣጠም ፤ የቦንብ አጠቃቀምና የመሳሰለውን ያሰለጠኗቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የእሥራኤል የስለላ ድርጅት(ሞሳድ) ሠራተኞች ናቸው ሲል «ሐዓሬትዝ» የተሰኘ በእስራኤል የሚታተም ጋዜጣ አስነብቧል። ይሁን እንጂ የኔልሰን ማንዴላ ድርጅት፤ በሰጠው መግለጫ፤ ከማንዴላ የግል ማኅደርም ሆነ ከሌላ ይህን ዜና የሚያረጋጋጥ አንዳች ፍንጭ እንደሌለ አስታውቋል። ከ 4 ዓመት ገደማ በፊት፤ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙ አንድ የኔልሰን ማንዴላ ድርጅት ዋና ተመራማሪ፤ ማንዴላን በማሠልጠን ያገዙ በሕይወት የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ ጠይቀው ያሰባሰቡት መረጃ ፣ ማንዴላ ከእሥራኤላውያን ጋር ግንኑነት እንደነበራቸው የሚያረጋግጥ አንዳችም እውነታ አልተገኘበትም። ታዲያ «ሐዓሬትዝ» የተሰኘው የእስራኤል ታዋቂ ጋዜጣ ይህንን መረጃ እንዴት ሊያወጣ ቻለ? ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ እስራኤል ለሚገኘው ወኪላችን ዜናነህ መኮንን ደውዬ ያቀረብኩለት ጥያቄ ነበር።


ዜናነህ መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች