አነጋጋሪው አዲሱ የብሪታኒያ የኢሚግሬሽን ህግ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አነጋጋሪው አዲሱ የብሪታኒያ የኢሚግሬሽን ህግ

በአዲሱ ህግ መሰረት ልጆቻቸውን ማስመጣት የሚፈልጉ ዜጎች ደግሞ በ ልጆች ቁጥር ከፍ የሚል በህጉ የተደነገገው ዓመታዊ ገቢ ሊኖራቸው ይገባል ። አዲሱ ህግ ቤተሰብ የሚለያይ ና ቤተሰብ የመመስረት መብትን የሚጋፋ ነው ሲሉ የመብት ተሟጋቾች አጥብቀው ተቃውመውታል ።

የብሪታኒያ መንግሥት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ውጭ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸውን ወደ ብሪታኒያ ለማምጣት ለሚፈልጉ የብሪታኒያ ዜጎች ያወጣው አዲስ  ህግ እያነጋገረ ነው ። አዲሱ ህግ  ዜጎች ፣ ባለቤቶቻቸውን ወደ ብሪታኒያ ለማስገባት የዓመት ገቢያቸው ቢያንስ 18 600 ፓውንድ እንዲሆን ደንግጓል ።  በአዲሱ ህግ መሰረት ልጆቻቸውን ማስመጣት የሚፈልጉ ዜጎች ደግሞ በ ልጆች ቁጥር  የሚጨምር በህጉ የተደነገገው ዓመታዊ ገቢ ማሳየት ይኖርባቸዋል ።  ህጉ ቤተሰብ የሚለያይ ና ቤተሰብ የመመስረት መብትን የሚጋፋ ነው ሲሉ  የመብት ተሟጋቾች አጥብቀው ተቃውመውታል ። የብሪታኒያ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ህግ ተጎጂ መሆናቸውን የለንደኗ  ወኪላችን የሃና ደምሴ ዘገባ ያስረዳል።    

ሃና ደምሴ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ              ሃና ደምሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ  

Audios and videos on the topic