አነጋጋሪዉ ግብረ ሰዶማዊ ባለስልጣን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አነጋጋሪዉ ግብረ ሰዶማዊ ባለስልጣን

ከዚህ ቀደም ጀርመን ዉስጥ ፆታቸዉ የተናጋ ተብለዉ በግብረ ሰዶም ይጠረጠሩ የነበሩት መልከ መልካም የፊልም ተዋንያን፤ የሙዚቃ ደራሲዎችና ዘፋኞች የመሳሰሉ ነበሩ ይለናል ከበርሊን የደረሰን ዘገባ።

default

ቬስተርቬለና ተጓዳኛቸዉ

ግን አሁን ጥናቶች እንደሚሳዩት በሠራዊቱ ዉስጥ፤ በመንግስት መስሪያ ቤት፤ በትምህርት ቤቶችና በሌሎችም መስኮች ግብረ ሰዶማዉያን ይገኛሉ። ወደፖለቲካዉ ዓለምም የገቡ ቁጥራቸዉ አንድ እና ሁለት አይደለም። ከእነሱ መካከል የበርሊኑ ከንቲባ አንዱ ሲሆኑ ሌላኛዉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቀዉ ጊ ዶ ቬስተርቬለ ናቸዉ። እኝህ ሰዉ ሚኒስትር ሆነዉ አፍሪቃም ሆነ እስያ ብቅ ሲሉ፤ አለያም ከአረብ መንግስታት መሪዎች ጋ ተገናኝተዉ ሲነጋገሩ ሌላዉ ዓለም ምን ይለናል የሚለዉ የሰሞኑ የጀርመኖች የመወያያ ርዕስ ሆኗል።

ይልማ ኃይለሚካኤል /ሸዋዬ ለገሠ/ተክሌ የኋላ