አነጋጋሪዉ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅምና አዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 14.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አነጋጋሪዉ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅምና አዲስ አበባ

ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የኦሮሚያን «ልዩ ጥቅም የሚያስጠብቅ» የተባለ ረቅቅ አዋጅ «ሾልኮ» ወጣ ተብሎ አወዛጋቢ ሰነድ ከተሰራጨ ወዲህ ወጣ ወዲህ በርካቶችን ማነጋገሩ እንደቀጠለ ነዉ። መንግሥት ወጣ የተባለዉን ረቂቅ ሰነድ «የማያዉቀዉ» እንደሆን ገልፆአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 31:52

ዉይይት፤ አነጋጋሪዉ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅምና አዲስ አበባ

በ 1987 ዓ.ም በፀደቀዉ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀፅ 5 መሰረት “የኦሮሚያ ክልል፤ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፤ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡” ይላል። በዝርዝር ይወጣል የተባለዉ ሕግ ይወጣል ተብሎ ሲጠበቅ ከ 20 ዓመት በላይ ቢሆነዉም፤ ጉዳዩ በየጊዜዉ እየተነሳ ከማወዛገብ በስተቀር እስካሁን ትክክለኛ ሕጋዊ መፍትሔን አላገኘም። ልዩ ጥቅም ሲባልስ ምንድን ነዉ? ይወጣል የተባለዉ ዝርዝሩ ሕግ ለምን እስካሁን ዘገየ? በዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸዉን እንዲያካፍሉን የጋበዝናቸዉ፤ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ፤ አቶ ሙላቱ ገመቹ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር፤ አቶ የሽዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፤ እንዲሁም የኢንተርኔት ፀሐፊዉ በፍቃዱ ኃይሉ ናቸዉ። አነጋጋሪዉ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅምና አዲስ አበባ በተሰኘዉ የዉይይት ዝግጅት ላይ  የተካፈሉትን ተወያዮች በዶይቼ ቬለ ስም እያመሰገንን ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ  

Audios and videos on the topic