አነጋጋሪዉ የአፋን ኦሮሞ ፊደል  | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 28.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

አነጋጋሪዉ የአፋን ኦሮሞ ፊደል 

ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ/ም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ልሳን የሆነዉ የኦሮሚያ ቴሌቭዥን የክልሉን ትምህርት ጽህፈት ቤት ጠቅሶ በትምህርት ጥራት ላይ ያለዉን ችግር ለመፈተሽ በተደረገዉ ጥናት የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች የአፍ-መፍቻ ቋንቋቸዉን ማንበብ እና መፃፍ ላይ ችግር እንዳለባቸው ገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:06

አፋን ኦሮሞ

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ጽህፈት ቤት ችግሩን ለማስወገድ ተማሪዎቹ በቀላሉ ማንበብ እና መፃፍ የሚያስችላቸው አዲስ የማስተማሪያ ዘዴ አዘጋጅቶ ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በተግባር አውሏል። ተግባር ላይ የዋለው የማስተማሪያ ዘዴ የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች በፊት ABCD(አባጫዳ) በሚል ሲማሩ የነበሩበትን የአፋን ኦሮሞን ፊደል አሁን LAGM(ላአጋማ) በሚል ተክቷል። 

ABCDን በመዋዕለ-ሕፃናት ተምረው ወደ አንደኛ ክፍል የገቡት ተማሪዎች በአዲሱ የማስተማሪያ ዘዴ እንደተደናገሩና ይህም ለአስተማሪዎችም ይህም ትልቅ ችግር መሆኑ ተገልጿል። ይህ ጉዳይ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከተሰራጨ በኋላ በሁለተ ጎራዎች የተከፈለ ከፍተኛ ክርክር ቀስቅሷል። የመጀመሪያው  ቡድን የአፋን ኦሮሞን ፍደል ቅድም-ተከተል ተቀይረዋል ፣ስለዚህ ወደ ቦታዉ ይመለስ የሚለው ሲሆን፣ ሌላው የፊደሉ ቅድም-ተከተል ሳይሆን የተቀየረው የማስተማርያ ዘዴ ብቻ ነው የሚለው ነው። የመጀመሪያው ቡድን በትዊተር ላይ #‎ABCDeebisaa‬ የተሰኘና #BringBackABCD የሚል ሃሽታግ በመጠቀም የፊደሉ ቅደም ተከተል እንዳይቀየር ዘመቻ አካሂደዋል። በሌላዉ ጎራ ደግሞ፣ በተለይም የክልሉ ትምህርት ጽህፈት ቤት፣ የአሜሪካዉ የርዳታ ድርጅት «USAID» በገንዘብ ባገዘዉ ጥናት ላይ የተሳተፉት ባለሙያዎች ተቀየረ በሚሉት የአፋን ኦሮሞ ፊደል ቅደም ተከተል ላይ መልስ ስሰጡ ይገኛሉ።

ጥናቱ ለምን ተካሄደ፣ ማን አካሄዴው፣ እንዴትስ ተካሄዴ?

የተባባሩት መንግስት እቅድ በሆነው የምዕተ-አመቱ የልማት ግቦች ዉስጥ ድህነት ቅነሳ አንዱ ነዉ። ለዚህም መሰረታዊ ትምህርት እንደ ጀርባ አጥንት ይቆጠራል።  ማንበብና መጻፍ  ለተማሪዎች በጣም አስፈላጊ ክሂሎት መሆኑን USAID  ጠቅሷል። 70 አገሮች USAID በ«Early Grade Reading Assesment /EGRA/» ዘዴ በመጠቀም በ120 ቋንቋዎች ላይ  የተማሪዎች የማንበብና የመጻፍ ችሎታ መፈተሻቸውን ዶክተር ቶላ ባርሶ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። እንደ አዉሮጳዉያኖቹ አቆጣጠር በ2010 ዓ/ም በኦሮሚያም የተማሪዎች የማንበብና የመጻፍ ክሂሎት በዚሁ ዘዴ ተፈትሾ ጥናት መካሄዱንም የአሮሚያ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ቶላ ይናገራሉ።  መቀመጫዉን ዩኤስ አሜሪካ ባደረገዉ ለReaserch Triangle Institute ከ«USAID» በተገኘዉ 90 ሚሊዮን ዶላር ያካሄደው ጥናት ኦሮሚያንና አድስ አበባን ጨምሮ ሌሎች ስድስት ክልሎች ላይ እንደተደረገ ዶክተር ቶላ ይናገራሉ።

ጥናቱ የገንዘብና የሌሎች ቁሳቁሶች ርዳታ የሚያስፈልገው ስለነበር የትምህርት ሚንስቴር  ጨረታ እንዲካሄድ ማስደረጉን  ዶክተር ቶላ አክሎበታል፣ «ይህ ጥናት የተካሄደዉ በ2ኛና በ3ኛ ክፍል የሚገኙት ተማሪዎች ላይ ነዉ። በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ 338 ትምህርት ቤቶች ተወስደው 13ሺህ 79 ተማሪዎች ላይ ጥናቱ ተደርጓል። በኦሮሚያም በ16 ዞን ዉስጥ በ63 ትምህርት ቤቶች  ላይ ጥናቱ ተካሂዷል።»

በዝህም ጥናት የተሳተፉት የአድስ አባባ ዩኒቬርስት መምህራኖች፣ ከአንደኛ እስከ አራተ ኛ ክፍል  ያሉት መምህራን፣ የትህምርት ጽህፈት ቤቶችና የመምሃራን ኮሌጆች ባለሙያዎች፣ መረጃ መሰብሰናቸውን ዶክተር ቶላ ይናገራሉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፋን ኦሮሞ ክፍለ-ትምህርት የስነ/ቋንቋ መምህር የሆኑት ዶክተር ቶላማርያም ፉፋ በዝህ ጥናት ላይ መሳተፋቸዉን ይናገራሉ። በጥናቱም ግዜ አምስት ይዘት ያለዉና ተማርዎች በቀላሉና ዉጤታማ በሆነ መንገድ ማንበብና መጻፍ የሚያስችላቸዉ Reading Based Mother Tongue Teaching የተባለዉን የማስተማርያ ዘዴ ስራ ላይ ማዋላቸውን ዶክተር ቶላማርያም ገልጸዋል።

እንደ ዶክተር ቶላማርያም ገለጻ፣ በቋንቋዎች ዉስጥ የትኛዉ ፊደል ተደጋግሞ እንደሚመጣ ወይም «frequency count» የሚለካ «ፕርምያር ፕሮ» የተሰኘዉን ሶፍትዌር ተጠቅመዋል። ከዜና፣ ከልበወለድ እንድሁም ከዝርው ጽሁፍ ከአራት ሺህ ያላነሱ ቃላት ወደዚህ ሶፍትዌር በማስገባት ተደጋግሞ የመጣዉን የፊደል ድምፅ፣ ከቀላል ወደ ከባድ ለመፃፍ እና ለማንበብም የሚያስችል የፊደል ምልክት በቅድም-ተከተል እንደሚያስቀምጥ ጠቅሰዋል። በዝህም መሰረት የተገኘዉ ዉጤት ለምሳሌ፣ በአፋን ኦሮሞ ፍደል ዉስጥ L ከ A በላይ ተደጋግሞ መጥቷል። ተደጋግመው በመጡት ፊደላት ላይ በመመርኮዝ ለአንደኛ ክፍል አዲስ መፅሃፍ መዘጋጀቱንም ይናገራሉ። በመጻፉም ላይ ተማሪዎች በፊት በሚመሩበት ABCD ፈንታ በ LAGM እንዲማሩ መደረጋቸዉን ዶክተር ቶላማርያም አክለውበታል።

ሆኖም፣ ይህን ግኝት ስህተቶች አሉት በሚል ባለሙያዎች ተችተውታል። ለምሳሌ አፋን ኦሮሞን ወደ ጎግል ትርጉም እንዲገባ እየሰራ ያለዉ Grand Afaan Oromo Project በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የባለሙያዎች ቡድን፣ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የአፋን ኦሮሞ ቃላትን በተመሳሳይ ሶፍትዌር ዉስጥ በማስገባት ያገኘዉ ዉጤት ፊደሎቹ ከL ሳይሆን ከA እንደሚጀምሩ በጽሁፋቸዉ ገልፀዋል። ይልቁንስ L በፊደል ተርታ ላይ  በ13ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠጠቅሰዋል።

የዚህ ፕሮጄክት አባል የሆኑት የስነ ቋንቋ ባለሙያ አቶ አማኑኤል ራጋ ይህ ዘዴ አለው ያሉትን ተጽዕኖ ለዶይቼ ቬሌ እንዲህ ገልጸዋል፥ «አንደኛ ተማሪዎች ይህን የተምታታ የፊደል ቅደም ተከተል  ተምረዉ ወደ ከፍተኛ ክፍል ሲሻገሩ ተመሳሳይ ፊደሎች የሚጠቀሙት የሌሎች ቋንቋዎች ፊደሎችም እንደዛዉ ሊመስሏቸዉ ይችላል። ሁለተኛዉ የዚህ የአዲሱ የቁቤ አፋን ኦሮሞ ታኣማኒነት ጥያቄ ዉስጥ ነዉ ያለዉ። እዉነት ይህ የቁቤ ችግር ነዉ ወይ የሚል ጥያቄ ማንሳት አለብን። ከዛ በተረፈ የቁቤ አፋን ኦሮሞ ከኦሮሞ ቀንቋ ታሪክና ከሕዝቡ ጋር የተገናኘ ነዉ። የአሮሞ ማንነት በዚህ ሰዓት የሚገለጸዉ ወይም ኦሮሞነትን ለመግለጽ የቀረዉ ነገር ካለ ቀንቋዉ ነዉ። ስለዚህ ይህን ከማንነት ጋር የተቆራኘ ነገር መነካካት አስፈላጊ አይደለም።»

የኦሮሚያ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ቶላ ግን LAGM የሚለው ቅደም ተከተል ለአንደኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የማስተማሪያ ዘዴ እንጂ ፣ የተለመደዉ ABCD የሚለውን የፊደል ቅደም-ተከተል የቀየረ አይደለም ይላሉ። አልተቀየረም ይላሉ። ግን ከባለምያዎች የተነሱ ችለትኝነት ትልቅ ችግር እንደነበረ ሳይጠቅሱ አላለፉም፣« የተለመደዉ ABCD አልተቀየረም፣ የተቀየረዉ የማስተማሩ ዘዴ ነዉ ብለህ ለማስረዳት ብትሞክር ሰው ግራ ሊገባው ይችላል። ተማሪዎችን መጀመርያ ABCD የሚለዉን እስከ መጨረሻ ድረስ ካስተማርክ በኋላ የማንበብና መጻፍ ማስተማርያ ዘዴ ነዉ የተባለዉን LAGM ብታስከትል ኖሮ  ችግር አልነበረም። ከL የሚጀምረዉን ፍደል ሰዉ በመጽሀፉ ሲመልከት የቁቤ አፋን ኦሮሞ ቅደም-ተከተል ተቀየረ የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱና መከራከሩ ትክክል ነበረ። ባለሙያዎችን ለምን ቀየራችሁት ተብለው ሲጠየቁም በመዋለ-ሕፃናት የተለመደዉን ፊደል ተምረው ስለሚመጡ የሚል መልስ ተሰጥቶ ነበር። ከከተማ ዉጭ በገጠር ያለዉ አብዛኛዉ ተማሪ መዋዕለ-ሕፃናት ስለሌለ የተለመደዉን ፊደል የት ተምረው ይመጣሉ ብዬ ጠይቃቸዉ ነበር።»

ጽህፈት ቤቱ ህብረተሰቡንና  አብዣኞቹን ባለሙያዎች ስለማስተማሩ ዘዴ አለማሳወቁን ዶክተር ቶላ እንደ ችግር ይቀበላሉ። በጥናቱ እና መጽሀፉን  በማሳተም አስተዋፅዖ የነበራቸዉ ዶክተር ቶላማርያም ዶክተር ቶላ ያቀረቡትን ሃሳብ ይጋራሉ።ባላፈዉ እሁድ የክልሉ ትምህርት ጽህፈት ቤት ብሮ ባለሙያዎችን በመሰብሰብ በአንድ ወር ዉስጥ መጻሃፉ እንዲገመገም የጎደለዉ እንዲሟላ ማመወያየቱን ለመረዳት ተችለዋል።

የስነ-ቋንቋ ባለሙያዉ አቶ አማኑኤል ራጋ ትምህርት ጽህፈት ቤቱ ሊያደርግ ያቀደዉን ለዉጥ ተቀብለው፣ ዉጤቱን ግን ቆይቶ የሚታይ ይሆናል ብለዋል።

መርጋ ዩናስ

አርያም ተክሌ


 

Audios and videos on the topic