አነጋጋሪዉ የሲቪል ትብብር በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 16.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አነጋጋሪዉ የሲቪል ትብብር በጀርመን

ዞልን ከባየርን ዋና ከተማ ከሙኒክ ትንሽ ፈንጠር ብላ የምትገኝ መንደር ናት። በዚች በፀዳችና ባማረች መንደር ደግሞ የተማሩና ከፍተኛ ገቢ ያላቸዉ የአገሪቱ ሰዎች እንደሚኖሩባት ይነገራል።

default

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በዚያ የተፈፀመዉ ድርጊት ግን ሰሚዎቹን ሁሉ አስደንግጧል። እንዲህ ነዉ የሆነዉ፤ ሁለት የ17እና 18 ዓመት ወጣቶች ሌሎችን ለመደብደብ ሲነሱ ለመገላገል የገባ አንድ ሰዉ ራሱ ተደብድቦ ሰዎች ባሉበት ስፍራ በቀን ብርሃን ህይወቱ አልፏል። ይህን ያስተዋሉ ዜጎች ታዲያ ልጆቻችን እየተባላሹ መጡ ቁጥጥርና ጠንከር ያለ ቅጣት ያስፈልጋል የሚል ጥሪያቸዉን አጠናክረዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል/ሸዋዬ ለገሠ ፣

ተክሌ የኋላ፣