አቶ ግርማ ሠይፉና መጪዉ ምርጫ | ኢትዮጵያ | DW | 12.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አቶ ግርማ ሠይፉና መጪዉ ምርጫ

ፓርቲዉ በምርጫዉ ለመሳተፍ አጩዎቹን ሰይሞ፤የመወዳደሪያ አላማዎቹን ለይቶ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ነበር።በዚሕ መሐል ነዉ ፓርቲዉ በአቶ ግርማ ቋንቋ «ለመወዳደር አይደለም ዉድድር ለመመልከት እንኳን ያልተዘጋጁ» ላሏቸዉ ሰዎች የተሰጠዉ።

በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዉ የተቃዋሚ ፓርቲ እንደራሴ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ በታቀደዉ ምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ።እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተቃዋሚዉን የኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በምክትል ፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት አቶ ግርማ እንደሚሉት በምርጫዉ የማይወዳደሩት የኢትዮጵያ መንግሥትና ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ በፓርቲያቸዉ ላይ ባደረሱባቸዉ ተፅዕኖ ነዉ።በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዉሳኔ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕን የፓርቲነት ፍቃድና ዕዉቅና ያገኙት ወገኞች በአቶ ግርማ እምነት አንድነትን የሚወክሉ አይደሉም።

መስከረም፤ 2003 ጀምሮ-ብቸኛ ከሚል ቅፅል ጋር የምክር ቤት እንደራሴነቸዉ ሲጠቀስ-ሲዘገብ እዚሕ ደረሱ።በሕጉ-መሠረት ያሉበት ምክር ቤት-በመጪዉ መስከረም በሌላ እስከሚተካም የምክር ቤት እንደራሴነታቸዉ ከነቅፅላቸዉ መቀጠሉ አይቀርም።አቶ ግርማ ሰይፉ።ከዚያ በሕዋላ ግንብቸኛ» የሚለዉን ቅፅል «የቀድሞዉ» በሚለዉ ለማስተካት እንደ ፖለቲካዉ ወግ በምርጫ ተወዳድረዉ እስኪሸነፉ ወይም ከፖለቲካዉ «ጡረታ» እሲከዉጡ አልጠበቁም።የ48 ዓመቱ ጎልማሳ በግንቦቱ ምርጫ-መወዳደሩን ይፈልጉታል ግን አይወዳደሩም።

«እኛ» የሚሉት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ን።ፓርቲዉ በምርጫዉ ለመሳተፍ አጩዎቹን ሰይሞ፤የመወዳደሪያ አላማዎቹን ለይቶ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ነበር።በዚሕ መሐል ነዉ ፓርቲዉ በአቶ ግርማ ቋንቋ «ለመወዳደር አይደለም ዉድድር ለመመልከት እንኳን ያልተዘጋጁ» ላሏቸዉ ሰዎች የተሰጠዉ።

1997 ምርጫ ዉጤት የቀሰቀሰዉ ደም አፋሳሽ ዉዝግብ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሕብረት፤ ጉልበትና እዉቅና አሳጥቶ በጣለ ማግሥት እንዳዲስ ከተደራጁት ፓርቲዎች ሰፊ ተቀባይነት፤ ብዙ አባላት ጠንካራ ፖለቲከኞችን ካሰባሰቡ ጥቂት የፖለቲካ ማሕበራት አንዱ-አንድነት ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፖለቲከኞች መካካል የተነሳዉን ክፍፍል አስታኮ ባሳለፈዉ ዉሳኔ ከተወዛጋቢዎቹ ለአንዱ አዉቅና ሰጥቷል።አቶ ግርማ «ክፍፍል» የሚለዉን አይቀበሉትም።ዉሳኔዉንም «ሕገ-ወጥ» ይሉታል።

547 በመቀመጫዎች ባሉት ምክር ቤት የተቃዋሚ ፓርቲ ብቸኛዉ ተወካይ በመሆን እስካሁን ያከናወኑትን ተግባር ጥሩ መጥፎነት አቶ ግርማ «ተመልካች ነዉ ፈራጁ ይላሉ።«ያቅሜን አድርጌያለሁ» አከሉ እንደራሴዉ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

 

 

 

Audios and videos on the topic