አቶ አንዳርጋቸው ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ና አውሮፓ | ኢትዮጵያ | DW | 12.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አቶ አንዳርጋቸው ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ና አውሮፓ

ደብዳቤው የእንግሊዝ የአሜሪካና የአውሮፓ ፓርላማ እንደራሴዎች የፈረሙበትና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:12
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:12 ደቂቃ

የአሜሪካና የአውሮፓ ባለስልጣናት ጥያቄ

የአሜሪካና የአውሮፓ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ መንግሥት ያሠራቸውን የተቃዋሚው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን እንዲፈታ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መላካቸው ተዘግቧል ።ደብዳቤው የእንግሊዝ የአሜሪካና የአውሮፓ ፓርላማ እንደራሴዎች የፈረሙበትና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። አቶ አንዳርጋቸው ከየመን ተወስደው ኢትዮጵያ ውስጥ ከታሰሩ አንድ ዓመት አልፏቸዋል ። ገበያው ንጉሴ ከብራስልስ ዘገባ አለው ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic