አቶ በቀለ ነጋ ቁም እስር ላይ ናቸው | ኢትዮጵያ | DW | 31.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አቶ በቀለ ነጋ ቁም እስር ላይ ናቸው

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በምኅፃሩ(ኦፌኮ)ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ መታመማቸው እየተነገረ ነዉ። እንዲያም ሆኖ አቶ በቀለ ገርባ ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውም ተሰምቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:50
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
01:50 ደቂቃ

የኦፌኮ አመራር አባላት ኅመምና የቁም እስረኝነት

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በምኅፃሩ (ኦፌኮ) ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ ደግሞ ዛሬ የእጅ ስልካቸው ተቀምቶ በቁም እስር እንደሚገኙም ተገልጧል። አቶ በቀለ ገርባ በጠና ታመዋል፤ ህክምናም ተከልክለዋል መባሉን በተመለከተ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ በስልክ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ከቤተሰባቸውም ሆነ ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን ጠቅሰዋል። የኦፌኮ ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ ደግሞ ዛሬ ጠዋት ስላካቸው ተቀምቶ «በቁም እስረኝነት» እንደሚገኙ ተገልጧል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic