አትሌቱ-የሮሙ ጀግና ታሪክ | ባህል | DW | 27.09.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

አትሌቱ-የሮሙ ጀግና ታሪክ

የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪቃን ልዩ ታሪክን ያዘለዉ የጀግናዉ የአበበ በቂላ የህይወት ታሪክ በተለይም ደግሞ የሩጫ ስፖርት ህይወቱን የሚተርከዉ አትሌቱ ወይም በእንግሊዘኛ መጠርያዉ The Athlete

የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪቃን ልዩ ታሪክን ያዘለዉ የጀግናዉ የአበበ በቂላ የህይወት ታሪክ በተለይም ደግሞ የሩጫ ስፖርት ህይወቱን የሚተርከዉ አትሌቱ ወይም በእንግሊዘኛ መጠርያዉ The Athlete የተሰኘዉ ፊልም እዚህ በጀርመን በኮለኝ ከተማ በሚገኝ ሲናማ ቤት ለህዝብ ታይቶአል። በ1960 ዎቹ የአፍሪቃዉያን የአሸናፊነት ምሳሌ በመሆን ፈር ቀዳጅ ሆኖ በዓለም የስፖርት መድረክ ብቅ ያለዉ ኢትዮጵያዊዉ አትሌት አበበ ቢቂላ ታሪኩ በዓለም ህዝብ ታዋቂ ቢሆንም ቅሉ፤ በኮለኝ አትሌቱ የተሰኘዉን ጥናታዊ ፊልምን ያዩ ነዋሪዎች በአበበ ቢቂላ የመንፈስ ጥንካሪ ቆራጥነት ዳግም ተደንቀዋል፤ ታሪኩም በፊልም መልክ ቀርቦ በዓለም ታሪክ ማህደር ለመብቃት መቻሉን ይበል ብለዋል። የሮሙ ጀግና የቶክዮዉ ኮከብ ጀግናዉ መቶ አለቃ አበበ ቢቂላ በጎ,አ 1968 ዓ,ም በጀርመን፣ ፍራንክፈርት ከተማ ላይ ከዶቼ ቬለ ራድዮ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር። እስቲ አትሌት አበበ ቢቂላ የዛሪ 44 ዓመት ምን አለ። ከድምጽ ማህደራችን የሰጠዉን ቃለ ምልልስ አግኝተናል በከፊል እናስደምጣለን።

የፍፊልም ስራ አዋቂዉ ኢትዮጵያዊዉ ራሴላስ ላቀዉና አሜሪካዊዉ አቻዉ ዴቢ ፍራንክል፤ ስለ ጀግናዉ ኢትዮጵያዊ አትሌት አበበ ቢቂላ የሚተርከዉን ፊልም አዘጋጅተዉ ለዓለም ህዝብ አሳይተዋል። ይህ ፊልም ወደ ጀርመን ዘግይቶ የመጣዉ ፊልሙን የሚገዛ ሰዉ ባለማግኘታቸዉ እንደነበር ኢትዮጳያዊዉ የፊልም ስራ አዋቂ ራሴላስ ላቀዉ ነግሮናል። በርግጥ ራሴላስ ወደ ጀርመን ባይመጣም አሜሪካዊ የስራ ባልደረባዉን ልኮአል

« ራስን ለመጀመርያ ግዜ ያወኩት ከአራት አመት ግድም በፊት ነዉ። ስለ አበበ ቢቂላ ታሪክ አወራን ታሪኩን በመጻፍ ረገድ ከተካፈልኩ በኃላ ከሶሶት አመት ግድም በፊት ይመስለኛል የፊልም ስራ ቀረጻዉን ጀመርን። የመጀመርያ ቀረጻዉንም በኢትዮጵያ ሳይሆን ኖርዊ ዉስጥ ነበር። ከዝያ ነዉ በሁለተኛዉ የቀረጻ ዙር ወደ ኢትዮጵያ ያቀናነዉ። ከዝያም ተመልሰን ገንዘብ አሰባስበን ሶፍያ ቡልጋሪያ ዉስጥ ቀረጻችንን አካሄድን። ከዝያም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰን ስራችን ቀጠልን» አሜሪካዊዉ የፊልም ስራ አዋቂ አትሌቱ የተሰኘዉን ፊልም ለተመልካች ከማሳየቱ በፊት የአበበ ቢቂላን ማንነት ፊልሙን የት አገር እንደተሰራ አጭር ማብራርያ ከሰጡ በኋላ ነበር ፊልሙ መታየት የተጀመረዉ። በርግጥ ይህ ፊልም ወደ ጀርመን የገባዉ ዘግይቶ መሆኑ እሙን ነዉ። ዴ ቪ በመቀጠል የአበበ ቢቂላ የተለየ እና ብቸኛዉ ኦሎምፒክ ታሪክን የሚያሳየዉ ጥናታዊ ፊልም በርካታ ሽልማቶችን እንዳገኘም ገልጸዉልናል።

« ይህ ፊልም በርግጥ በአለም ዙርያ በተደረጉ፤ በተለያዩ የፊልም ፊስቲቫሎች ቀርቦአል፤ በርካታ ሽልማቶችንም አግኝቶአል፤በተለያዩ አገራት፣ ኢትዮጵያንም ጨምሮ ታይቶአል»

Abebe Bikila Sportler Äthiopien 1960

የ1960ዉ የሮማዉ ኦሎምፒክ ድል ባለቤት አበበ ቢቂላ

አትሌት አበበ ቢቂላ ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ በጃቶ ተወለደ፤የባላዊዉን ትምህርት ዳዊትን ጨርሶአል፤ በፊልሙ ላይ እንደተገለጸዉም እንጊሊዘኛ ባይናገርም በመጠኑ ይገባባ፤ ቋንቋዉም ይገባዉ ነበር። አበበ በአስራ ሰባት አመት እድሜዉ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ለዉትድርና ተቀጠረ፤ ከዝያም ለንጉሰ ነገስቱ የክቡር ዘበኛ ሆኖ ማገልገል ጀመረ። አበበ በክቡር ዘበኛ ከተቀጠረ በኋላ የዉትድርና ስራዉ በሚያደርገዉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወደ ስፖርቱ አለም እንዳመጣዉ፤ ዘገባዎች ያሳያሉ። በዝያዉ በዉትድራና ተግባር ላይ ከተሰማራ ከሶስት አመት በኃላ በተደረገዉ አመታዊ የስፖርት ዉድድር ሩጫን ተወዳድሮ በአመርቂ ዉጤት በማስመዝገቡ ፤ በኦኒ ኒስካን አሰልጣኙ እንዲሁኑ ተደረገ እኚህ የስዊድን ዜጋ በትምህርት ሚኒስቴር ስር የአትሌቲክስ ተጠሪ በመሆኑ በኢትዮጵያ ማገልገላቸዉ ይታወቃል። አትሌት አበበ ለመጀመርያ ግዜ በአለም አቀፍ መድረክ ለዝያዉም በጣልያን ሮማ ላይ በሚካሄደዉ የኦሎምፒክ ዉድድር ለመካፈል ተመረጠ። ለሮማዉ ዉድድር አበበ በኢኒ ኒስካር አሰልጣኝነት በጥንካሪ ተዘጋጅቶአል። የነበሩት አገርን ወክሎ በአለም አቀፍ መድረክ እንዲወዳደር እድርጎታል። የአበበ ቢቂላ ሮማዉ ኦሎምፒክ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ አልነበረም፤ በዝያን ግዜ በምዕራባዉያን በቅኝ ግዛት ተይዞ ለአለዉ የአፍሪቃ ህዝብ ጭምር እንጂ። በኮለኝ 20 አመታትን ያስቆጠረዉ የአፍሪቃ ፊልም ፊስቲቫል ተጠሪ ካርል ሮስል በየአመቱ በምናዘጋጀዉ መድረክ ላይ የኢትዮጳያ ፊልሞች እንብዛም አልነበሩም ነገር ግን ባለፉት አመታት በመድረካችን ብቅ ማለት ጀምረዋል ሲሉ ይገልጻሉ

«ለፊልም ስራ ጉዳይ በርካታ ኢትዮጵያዉያን የፊልም ሰራተኞች እዚህ ተገኝተዋል። ለምሳሌ በጋና የፊልም ስራን ያጠና አንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ የፊልም ስራ አዋቂ፤ እዚህ መቶ አስተምሮአል። ሌላዉ በኢትዮጳያ ታዋቂ የሆነዉ የፊልም ስራ ጠበብት ሃይሌ ገሪማም እንዲሁ በየግዜዉ ይመጣል፤ ባለፈዉ ሳምንትም አዲስ እየሰራ ያለዉን የፊልም ይዘት ሊነግረን እዚህ ተገኝቶ ነበር። የጀመረዉ ፊልም ሲጠናቀቅ በመድረካችን ለህዝብ እይታ እንደምናበቃዉ ከአሁኑ መናገር እወዳለሁ። እና ቢሆንም ከምዕራብ አፍሪቃ ወደዚህ እንደሚመጣዉ የፊልም ስራ አዋቂና ፊልም ብዛት ባይሆንም ከኢትዮጳያ ፊልሞችን ባማሳየት ላይ እንገኛለን»የአትሌት አበበ ቢቂላን ታሪክ ለመስራት ከአስራ አምስት አመት በላይ ሲያወጣ ሲያወርድ የኖረዉ ኢትዮጲያዊ የፊልም ስራ አዋቂ ራሴላስ ላቀዉ ፊልሙን ለጀርመናዉያን ለማሳየት እዚህ ኮለኝ ከተማ ባይመጣም በሚኖርበት ኒዮርክ ላይ አግኝተነዋል። ሙሉ ቅንብሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 27.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16G4J
 • ቀን 27.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16G4J