አባ ሙሴ እና የበጎ አድራጎት ሥራቸው | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አባ ሙሴ እና የበጎ አድራጎት ሥራቸው

በሺህዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የሚረዱት የ40 ዓመቱ አባ ሙሴ እጎአ ለ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማት ከታጩት ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ተዘግቧል ። አባ ሙሴ ለዚህ ሽልማት መታጨታጨታው ክብሩ ለርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃውያንም ጭምር ነው ይላሉ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:06
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
11:06 ደቂቃ

አባ ሙሴ ዘርዐይ

አባ ሙሴ ዘርዐይ እዚህ አውሮፓ በመንፈሳዊ አገልግሎት የተሰማሩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሃይማኖት አባት ናቸው ። በአሁኑ ጊዜ ስዊዘርላንድ ለሚኖሩ ኤርትራውያን ኢትዮጵያውያን ካቶሊኮች መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው ። ከዚያም ቀደም ሲል በቀሰሱበት ና ከፍተኛ ትምህርታቸውን በተከታተሉባት በኢጣልያ ተመሳሳይ አገልግሎት ላይ ነበሩ ። ከዛሬ 9 ዓመት ወዲህ ደግሞ በመንፈሳዊው አገልግሎት ብቻ ሳይወሰኑ በግበረ ሰናይ ድርጅታቸው አማካይነት በሜዲቴራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ አፍሪቃውያን እየታደጉ ነው ። የዛሬ 23 ዓመት በመጡበት በኢጣልያ የመሰረቱት ኤጀንስያ አበሻ የተሰኘው ይኽው ድርጅታቸው በአደገኛ የባህር ጉዞ የሚሰደዱ በርካታ ወጣቶችን ህይወት አትርፏል። እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ስደተኞች ልዩ ልዩ ድጋፎችን በመስጠት ላይ ይገኛል ።
ምንም እንኳን አባ ሙሴ ኤጀንስያ አበሻን በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር 2006 ዓም ቢያቋቁሙም ስደተኞችን መርዳት የጀመሩት ግን ከዚያ አስቀድሞ ነበር።ድርጅታቸው ኤጀንሲያ አበሻ እነዚህን ሥራዎች የሚያከናውነው በበጎ ፈቃደኖች አገልግሎት ና የገንዘብ እርዳታ እንደሆነ አባ ሙሴ ያስረዳሉ ።ርሳቸው እንደሚሉት ድርጅታቸው ከመንግሥትም ሆነ ከትላልቅ ድርጅቶች ያሚያገኘው ገንዘብ የለም ። አባ ሙሴ ተወልደው ያደጉት የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አስመራ ኤርትራ ነው ። በጎርጎሮሳውያኑ 1992 ዓም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ቪዛ ካገኑ በኋላ በ17 ዓመታቸው ጣሊያን ይኖሩ ወደ ነበሩት አባታቸው ሄዱ ። በጣልያን ለተወሰኑ ዓመታት እየሰሩም እየተማሩም ከቆዩ በኋላ 26 ዓመት ሲሞላቸው ቅስና ተቀብለው ገዳም ገቡ ። የገዳም ህይወትን ከመረጡ በኋላ ዩኒቨርስቲ በመግባት ትምህርታቸውን ቀጥለው በፍልስፍናና በስነ መለኮት የባችለር ዲግሪ አግኝተዋል ። ከዚያም በመቀጠል በስነ መለኮት ትምህርት ስር የማህበራዊና የሞራል ትምህርትም ተከታትለዋል ። አባ ሙሴ እንደሚሉት መንፈሳዊው ህይወት ውስጥ የመግባት ፍላጎቱ የነበራቸው ገና ታዳጊ ወጣት ሳሉ አንስቶ ነበር ።
አባ ሙሴ ከጎርጎሮሳዊው 2006 ዓም ወዲህ ይበልጡን የሚታወቁት በበጎ አድራጎት ተግባራቸው ነው ። ርሳቸው እንደሚሉት ይሄ ከተሰማሩበት መንፈሳዊ አገልግሎት ተለይቶ የሚያታይ አይደለም።
በሺህዎች የሚዎጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የሚረዱት የ40 ዓመቱ አባ ሙሴ እጎአ ለ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማት ከታጩት ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ተዘግቧል ። አባ ሙሴ ለዚህ ሽልማት መታጨታጨታው ክብሩ ለርሳቸው ብቻ
በአሁኑ ጊዜ በአደገኛ የባህር ጉዞ ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ ሰዎችን ለመርዳት የሚደረገው ጥረት ቀድሞም ተጀምሮ ቢሆን የበርካታ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ይቻል ነበር ይላሉ አባ ሙሴ ። ወደፊት መንግሥታት ችግሩን ለመፍታት ይበልጥ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል ።

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic