አቡነ ማትያስ በእየሩሳሌም | ኢትዮጵያ | DW | 04.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አቡነ ማትያስ በእየሩሳሌም

መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛውን ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት የአቡነ ማትያስን በዓለ ሲመት ትናንት አከናውኗል። መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው እና ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሆነ የሚገልፀው ሌላኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የፓትርያሪክ ምርጫውን አዉግዟል።

default

ትግራይ ውስጥ ሀፀራ በምትባል መንደር የተወለዱት አቡነ ማትያስ ወደ መንበሩ ሲመጡ በመንግስት ተፅዕኖ ነው ሲሉም ተቃውሞዋቸውን የሚያሰሙ አሉ። የአዲሱ ፓትሪያርክ ሲመት የተከናወነዉ ሁለቱን ወገኖች ለማስማማት ለሶስት ዓመታት የተጀመረዉ የእርቀ ሠላም ጥረት ከግብ ሳይደርስ ነዉ። አቡነ ማትያስ በእየሩሳሌም ሳሉ የነበራቸው አስተዳደር ምን ይመስል ነበር? ወደ ፊትስ ለቤተክርስቲያኒቱ አንድነት ምን ሊያበረክቱ ይችላሉ? የሃይፋዉ ወኪላችን ግርማው አሻግሬ ከእየሩዳሌም የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል።   

ግርማው አሻግሬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic