አቃቢተ ህግ ቤንሱዳ ቃለ መሃላ ፈፀሙ | አፍሪቃ | DW | 15.06.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አቃቢተ ህግ ቤንሱዳ ቃለ መሃላ ፈፀሙ

ጋምባያዊቷ ፋቱ ቤንሱዳ ለአለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት በእንግሊዘኛው ምህፃር የICC ጠቅላይ አቃቢተ ህግነት ዛሬ ቃለ መሃላ ፈፀሙ ። ዘ ሄግ ኔዘርላንድስ ውስጥ በተካሄደው የቃለ መሃላ ስነ ስርዓት ላይ የ51 ዓመትዋ ቤንሱንዳ የአቃቢተ

Gambian war crimes lawyer Fatou Bensouda takes the oath to become the new prosecutor of the International Criminal Court (ICC) during a swearing-in ceremony at The Hague in the Netherlands June 15, 2012. Bensounda replaces Luis Moreno-Ocampo of Argentina. REUTERS/Bas Czerwinski/Pool (NETHERLANDS - Tags: CRIME LAW POLITICS)

ፋቱ ቤንሱዳ

ህግ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል ።

Fatou Bensouda, stellvertretende Chefanklägerin beim Internationalen Strafgerichtshof, Den Haag; Veranstaltung 21. September 2010, Berlin: Alles was recht ist - Internationale Strafgerichtsbarkeit in Afrika

እጎአ ከ 2004 ዓም አንስቶ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሉዊስ ሞሬኖ ኦካምፖ አስረክበዋል ። ቤንሱዳ የአለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ና አፍሪቃዊት አቃቢተ ህግ ናቸው ። የሥራ ዘመናቸውን ፈፅመው ዛሪ ሃላፊነታቸውን ለቤንሱዳ አስረክበዋል ። ቤንሱዳ የአለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ና አፍሪቃዊት አቃቢተ ህግ ናቸው ። ለዚህ ሥልጣን የበቁትም ፍርድ ቤቱ የተመሰረተበትን የሮሙን ውል በፈረሙ 121 ሃገሮች ተመረጠው ነው ። አቃቢተ ህግ ቤንሱዳ የዘር ማጥፋት፣ የጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ክስ የተያዙባቸውን የ 7አፍሪቃ አገሮች 15 ጉዳዮችን የመርመር ሃላፊነት ተረክበዋል ። እጎአ በ2003 የተቋቋመው ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት እስካሁን 20 የእስር ማዘዣዎችን ቢቆርጥም እስካሁን የታሰሩት ግን 6 ተጠርጣሪዎች ብቻ ናቸው ። በፍርድ ቤቱ ከሚፈለጉት ውስጥ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ና የጌታ ተከላካይ ጦር የተባለው የኡጋንዳውየአማፅያን ቡድን መሪ ጆሴፍ ኮኒ ይገኙበታል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

 • ቀን 15.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15GCJ
 • ቀን 15.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15GCJ