አሸባብ ጥቃት አደረሰ | አፍሪቃ | DW | 10.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አሸባብ ጥቃት አደረሰ

በሶማሊያ የሚግኝዉ እና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙንት እንዳለዉ የሚነገርለት ደፈጣ ተዋጊዉ ሃይል አሽባብ ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ባካሄደው የጥቃት ዘመቻ ከመቶ የሚበልጡ ተዋጊዎች መገደላቸውን ከሁለቱም ጦር ምንጮችና ከዓይን ምስክሮች የተገኘ ዜና አመለከተ።

በሶማሊያ የሚግኝዉ እና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙንት እንዳለዉ የሚነገርለት ደፈጣ ተዋጊዉ ሃይል አሽባብ ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ባካሄደው የጥቃት ዘመቻ ከመቶ የሚበልጡ ተዋጊዎች መገደላቸውን ከሁለቱም ጦር ምንጮችና ከዓይን ምስክሮች የተገኘ ዜና አመለከተ። ከዓይን ምስክሮቹ አንዱ አቡካር-ሞአሊም-ያሮው ለፈረንሣይ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ዩርኩት በተሰኘችው ማዕከላዊት መንደር የተካሄደው ውጊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች ባለፈው ሕዳር ወር ሶማሊያ ከገቡ ወዲህ ከባዱ መሆኑ ነው። የአካባቢው የዓማጺያኑ ጦር ከፍተኛ አዛዥ ሼይክ-ሞሐመድ-አቡ-ፋትማ ለዜና አገልግሎቱ በስልክ በሰጡት መግለጫ ሃይላቸው የጠላት ጦር በጊዜያዊንነት ሰፈሮቹን እንዲለቅ ማስገደዱንና ከአርባ የሚበልጡ የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉንም አስረድተዋል። የሶማሊያ መንግሥት ደጋፊ የሆኑት የባይዶዋ ባለሥልጣን ካሊፍ አዳን ደግሞ በአንጻሩ በርካታ የአሽባብ ተዋጊዎች መገደላቸውንና ቡድኑ ከባድ ሽንፈት እንደደረሰበትም ተናግረዋል። ከአስራ ስምንት ቀናት ግድም በፊት በሶማልያ የሰፈረዉ የኢትዮጵያ ጦር የደቡባዊ ሶማልያ ሥልታዊ ከተማ ባይዶዋን መቆጣጠሩ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ጦር ወደ ባይዶዋ ከመቃርቡ በፊት ከተማይቱን ጥሎ የወጣዉ አሸባብ የኢትዮጵያን ጦር እንደሚበቀል መዛቱም አይዘነጋም። በሌላ በኩል የዛሪ ሁለት ሳምንት ግድም ለንደን ላይ በሶማልያ ጉዳይ ላይ የተካፈሉት የሶማልያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዲወሊ መሐመደ ዓሊ፥መንግስታቸዉ እና የመንግስታቸዉ ረዳት አገራት ጦር የሚወጋዉ አሸባብ በወራት እድሜ እንደሚጠፋ ተስፋ እንዳላቸዉ መናገራቸዉ ይታወሳል። ኢትዮጵያና ኬንያ የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት በአፍሪቃ ሕብረት የሰላም ተልዕኮ በአሚሶም እየተረዳ አሸባብን ለማስወገድ በሚያደርገው ትግል ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። ሶማልያ በጦርነት እና በርሃብ ተወጥራ፣ ፍቱን የሆን ማዕከላዊ መንግስት ማቆም አቀቶአት ስርዓተ-ዓልባ ከሆነች ከሁልት እስርተ አመታት በላይን አስቆጥራለች።

አዜብ ታደሰ

መስፍ መኮንን

 • ቀን 10.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14IqV
 • ቀን 10.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14IqV