አስጊው የእስራኤል ዛቻ እና ሀማስ | ዓለም | DW | 01.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

አስጊው የእስራኤል ዛቻ እና ሀማስ

በምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በምትገኘው የሄብሮን ከተማ አቅራቢያ ከሁለት ሳምንት ተኩል በፊት የታገቱት የሶስት ወጣት እስራኤላዉያን አስከሬን ትናንት በዚያው መገኘቱን የእስራኤል መንግሥት አረጋገጠ። በእስራኤል መንግሥት ዘገባ መሠረት፣

ወጣቶቹን ከታገቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነበር የተገደሉት፤ ለዚሁ ግድያም እስራኤል የሃማስ ድርጅትን ተጠያቂ አድርጋለች። የወጣቶቹ አስከሬን ከመገኘቱ በፊት፣ የእስራኤል ጦር ኃይል ወጣቶቹን ፍለጋ ባለፉት ቀናት በምዕራባዊ ዳርቻ የተጠናከረ ፍተሻ ማካሄዱ የሚታወስ ነው። በዚሁ ወቅት በተፈጠረ ግጭት አምሥት ፍልሥጤማውያን ተገድለው በርካቶች ቆስለዋል። ወደ 420 ፍልሥጤማውያንም ታስረዋል። የወጣቶች አስከሬን ከተገኘ ወዲህ እስራኤል ገዳዮቹን እስክትይዝ ድረስ እንደማታቆም በማስታወቅ ጠንካራ አፀፋ ርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች። ይህም ባካባቢው አዲስ የፀጥታ ችግር እንዳይነሳ ብዙዎች ሰግተዋል። ስለዚሁ ወጣቶቹ መገደልና በሰበቡ ስለተፈጠረው ስጋት ኢየሩሣሌም የሚገኘዉን ዘጋቢያችንን ዜናነህ መኮንን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ዜናነህ መኮንን

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic