አስደንጋጩ የጀርመን አዉሮፕላን አደጋ መንስዔ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አስደንጋጩ የጀርመን አዉሮፕላን አደጋ መንስዔ

በደቡብ ፈረንሳይ በሚገኘዉ ተራራማማ አካባቢ ሰሞኑን የተከሰከሰዉ የጀርመን አዉሮፕላን በቴክኒክ ጉድለት ወይም በሌላ ምክንያቶች ሳይሆን ረዳት አብራሪዉ ሆን ብሎ የፈፀመዉ የጥፋት ርምጃ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ የ144 ተሳፋሪዎችና የ6 የበረራ ሠራተኞችን ሕይወት ያጠፋዉን የአደጋ መንስኤ የፈረንሳይና የጀርመን ፖሊሶች እንዲሁም አቃቤ ሕጉም ጭምር ባካሄዱት ምርመራ መሆኑ ተገልጿል። ይህ ምክንያት ሲሰማም በጀርመን ሕዝብ ዘንድ ዳግም ከፍተኛ ድንጋጤና ቁጣን ቀስቅሷል። ሆኖም ግን ድርጊቱ የሽብር ተግባር እንዳልሆነ የጀርመን መንግሥት የሀገር ዉስጥ አስተዳደር ሚኒስቴር በእርግጠኝነት አስታዉቆአል። የ 27 ዓመቱ ረዳት አብራሪ በመንፈስ መረበሽና ጭንቀት በሽታ ተጠምዶ እንደነበር አንዳንዶች ለብዙኃን መገናኛ ገልፀዋል። ዝርዝሩን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ልኮልናል።


ይልማ ኃይለሚካኤል


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic